ጆ ባይደን ትራምፕን “የአየር ንብረት ለውጥ አቀጣጣይ” ሲሉ ትራምፕ “ሳይንስ ስለ አየር ለውጥ የሚያውቅ አይመስለኝም” ብለዋል
የአየር ንብረት ለውጥ የትራምፕ እና የባይደን ወቅታዊ የምርጫ ፉክክር አጀንዳ ሆኗለ
በአሜሪካ 3 ግዛቶች ማለትም በካሊፎርኒያ ፣ ኦሪጎን እና ዋሽንግተን በአውሮፓውያኑ ከነሐሴ ወር ጀምሮ ከ 1 ወር በላይ በዘለቀው የሰደድ እሳት እስካሁን በትንሹ 36 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ከ100 በላይ በሚሆኑ ስፍራዎች የተነሳው የሰደድ እሳቱ 2 ሚሊዮን ያህል ቦታ ያቃጠለ ሲሆን ትንንሽ ከተሞችን ያጠቃ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን አቃጥሏል፡፡
ይህን ክስተት በተመለከተ ንግግር ያደረጉት በቀጣዩ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዴሞክራቶች እጩ ጆ ባይደን ተቀናቃኛቸውን ዶናልድ ትራምፕን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡
ጆ ባይደን
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለዓለም ሙቀት መጨመር እውቅና አለመስጠታቸው አሜሪካን ለአደጋ እያጋለጣት ስለመሆኑ በማንሳት ዶናልድ ትራምፕን “የአየር ንብረት ለውጥ አቀጣጣይ (ተቃዋሚ)” ብለዋቸዋል፡፡ ትራምፕ ለሳይንሳዊ እውነታዎች ትኩረት ማድረግ እንደነበረባቸውም ባይደን ተናግረዋል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው “ሳይንስ ስለአየር ንብረት ያውቃል ብዬ አላስብም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የቃጠሎው መንስኤ ከደኖች አስተዳደር ችግር እንደሆነ ነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የገለጹት፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ከሚደረገው ዓለም አቀፍ ስምምነት ማስወጣታቸው ይታወሳል፡፡