ትራምፕ በድጋሚ የምርጫውን ውጤት ለመቀየር ሊሞክሩ ይችላሉ የሚል ስጋት ተፈጠረ
በብሔራዊ ደረጃ እና ከፍተኛ ክፍፍል ባለባቸው ሰባት ግዛቶች የተሰበሰበው የህዝብ አስተያየት ትራምፕ እና ሀሪስ ከባድ ፉክክር እንደሚያደርጉ ያሳያል
የምርጫ 2020 ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ውጤት እንዲቀለበስ የፈለጉ የትራምፕ ደጋፊዎች በካፒቶል ሂል አመጽ ማስነሳታቸው ይታወሳል
የአሜሪካ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በድጋሚ የምርጫውን ውጤት ለመቀየር ሊሞክሩ ይችላሉ የሚል ስጋት ተፈጠረ።
በፔንስልቬንያ የመራጮች መረጃ ተጭበርብሯል በሚል የተሳሳተ መረጃ ያቀረቡት የሪፐብሊካኑ ፕሬዝደንታዊ እጩ ትራምፕ የምርጫውን አሸናፊ ለመወረን በእዚያ ወይም ጠንካራ ፉክክር በሚካሄድበት ሌላ ግዛት የሚካሄደውን ምርጫ ውጤት በድጋሚ ለመቀየር ሊሞክሩ ይችላሉ ተብሏል።
በብሔራዊ እና ከፍተኛ ክፍፍል ባለባቸው ሰባት ግዛቶች የተሰበሰበው የህዝብ አስተያየት አራት ቀናት በቀሩት ምርጫ ትራምፕ እና ሀሪስ ከባድ ፉክክር እንደሚያደርጉ ያሳያል።
ትራምፕ ተጨባጭ መረጃ ባያቀርቡም፣ በ2020 በተካሄደው ምርጫ በዲሞክራቶች የተሸነፉት፣ በተሸነፉባቸው ግዛቶች በነበሩ መጠነሰፊ ማጭበርበሮች መሆኑን አሁንም እየተናገሩ ነው። ትራምፕ እና ደጋፊዎቻቸው በፔንስልቬንያ በሚካሄደው የዘንድሮው ምርጫም የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ ነው ተብሏል።
ምርጫ 2020 ተከትሎ ስለምርጫ መጭበርበር የነበሩት ዘመቻዎች፣ የምርጫው ውጤት እንዲቀለበስ የፈለጉ የትራምፕ ደጋፊዎች በጥር 6፣2021 በካፒቶል ሂል አመጽ እንዲያስነሱ አደርጓቸዋል።
"ይህ ትራምፕ ያላሸነፉበትን ምርጫ ውጤት ለመቀልበስ ሙከራዎችን የመዝራት ተግባር ነው" ሲሉ 'የፕሮቴክት ዲሞክራሲ' አድቮኬሲ ቡድን የፖሊሲ ስትራቴጂስት ከይሌ ሚለር ተናግረዋል።
"በ2020 አይተነዋል፤ እናም ከእዚያ ጀምሮ ትራምፕ እና ደጋፊዎቻቸው የተማሩት እነዚህን ሀሳቦች ቀድሞ መዝራት እንዳለባቸው ነው።"
ትራምፕ ባለፈው ሀሙስ እለት ከመራጮች ፎርም ጋር በተያያዘ ተጨባጭ ያልሆነ መረጃ አሰራጭተዋል ተብሏል።
የግዛቱ ባለስልጣናት እና የዲሞክራሲ ተሟጋቾች ሲስተሙ በተፈለገው መልክ እየሰራ ነው ብለዋል።
የግዛቱ ባለስልጣናት በላንካስተር እና ዮርክ የምርጫ ጣቢያዎች የተጭበረበረ የሚመስል ምዝገባ ማግኘታቸው፣ የህግ አስፈጻሚ አከላት ምርመራ እንዲጀምሩ አስገድጇቸዋል። ነገርግን ምዝገባዎች ህጋዊ ወደአልሆነ ድምጽ የሚቀየሩበት ምንም መረጃ የለም ተብሏል።
"ይህ በመራጮች ምዝገባ ሂደታችን ውስጥ ያሉት የደህንነት መጠበቂያዎች እንደሚሰሩ የሚጠቁም ነው"ብለዋል ፔንስልቬንያ ከፍተኛ የምርጫ ባለስልጣን።
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ ኢኮኖሚ እና የሰደተኞች ጉዳይ እንዲሁም የአለምን የኃይል አሳላለፍ ላይ ተጼጽኖ ሊኖረው ይችላል የተባለው ምርጫ በመጭው ማክሰኞ ይካሄዳል።