ኢራን ዶናልድ ትራምፕን ለመግደል እያሴረች ነው ሲል የአሜሪካ ስለላ ድርጅት አስጠነቀቀ
የአሜሪካ ስለላ ድርጅት ስለ ኢራን ጥቃት ለዶናልድ ትራምፕ ማብራሪያ ሰጥቷል
ኢራን ከአሜሪካ ስለላ ድርጅት የቀረበባትን ክስ ውድቅ አድርጋለች
ኢራን ዶናልድ ትራምፕን ለመግደል እያሴረች ነው ሲል የአሜሪካ ስለላ ድርጅት አስጠነቀቀ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ከአንድ ወር በኋላ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ትገኛለች፡፡
በዚህ ምርጫ ላይ እጩ የሆኑት የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ዋነኛው ሲሆኑ በምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያሉ ሁለት ጊዜ የመግደል ሙከራ ተፈጽሞባቸዋል፡፡
አሁን ደግሞ ኢራን ዶናልድ ትራምፕን ለመግደል እያሴረች መሆኑን የአሜሪካ ስለላ ድርጅት አስታውቋል፡፡
የሀገሪቱ የስለላ ድርጅት ኢራን እያደረገች ስላለው ጥረት ለዶናልድ ትራምፕ ማብራሪያ መስጠታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የኢራን መረጃ ጠላፊዎች የትራምፕን የምርጫ ዘመቻ መረጃ ለተቀናቃኛቸው ባይደን ማቀበላቸው ተሰማ
የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን የኮሙንኬሽን ዳይሬክተር ስቴቨን ቼንግ አንዳሉት “የአሜሪካ ብሔራዊ ስለላ ድርጅት ዳይሬክተር ኢራን እያደረገች ስላለው ዝርዝር እቅድ እና ጥረት ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተውናል፣ ኢራን በአሜሪካ አለመረጋጋት እና ቀውስ እንዲመጣ እየሰራች መሆኗን ተረድተናል” ብለዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም የጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ደህንነት ለመጠበቅ በቅንጅት እየሰሩ መሆናቸውን እንደነገሯቸውም ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡
ኢራን በበኩሏ ዶናልድ ትራምፕን ለመግደል እያሴረች ነው መባሏን በይፋ ውድቅ ያደረገች ሲሆን በተለይም ዶናልድ ትራምፕ በፔንሲልቫኒያ በምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያሉ ተኩሶ ካቆሰላቸው ግለሰብ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለኝም ብላለች፡፡
የአሜሪካ ስለላ ተቋማት በበኩላቸው ኢራን የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን መረጃዎችን እንደመዘበረች በይፋ ተናግረዋል፡፡
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ላይ እያሉ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጦር አዛዥ የነበሩት ጀነራል ሱሌማኒ በባግዳድ እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል በሚል ቴህራን የእስራ ማዘዣ ማውጣቷ ይታወሳል፡፡