አሜሪካ በተመድ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በመቃወም ሳትጠበቅ ሩሲያን ደገፈች
አሜሪካ በዩክሬንና አውሮፓውያን የሚደገፈውን የውሳኔ ሀሳብ በመቃወም ከረጅም ጊዜ አጋሮቿ ጋር ሆድና ጀርባ ሆናለች

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችው ወታደራዊ ዘመቻ የከፈተችበት ሶስተኛ አመት በትናንትናው እለት ታስቧል
አሜሪካ በተመድ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በመቃወም ሳትጠበቅ ሩሲያን ደገፈች።
አሜሪካ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በትናንትናው እለት የቀረበውን ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን "ወረራ" የሚያወግዝ የውሳኔ ሀሳብ በመቃወም ባልተጠበቀ ሁኔታ ለሩሲያ ድጋፏን አሳይታለች።
አሜሪካ በዩክሬንና አውሮፓውያን የሚደገፈውን የውሳኔ ሀሳብ በመቃወም ከረጅም ጊዜ አጋሮቿ ጋር ሆድና ጀርባ ሆናለች።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችው ወታደራዊ ዘመቻ የከፈተችበት ሶስተኛ አመት በትናንትናው እለት ታስቧል።
አሜሪካ በተመሳሳይ ትናንት ምሽት ሩሲያን እንደ ወራሪ የማያየውንና ለዩክሬን የግዛት አንድነት እውቅና የማይሰጠውን በአሜሪካ ድጋፍ የተዘጋጀውን በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በመደገፍ ከሩሲያ ጋር አንድ አይነት አቋም አንጸባርቃለች።
ይህ የውሳኔ ሀሳብ የጸደቀው አምስት የአውሮፓ ቋሚ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ሳይደግፉት ነው።
አሜሪካ በተመድ ለአውሮፓውያን አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ ከሩሲያ ጋር ያበረችው የትራምፕ አስተዳደር ጦርነቱን በማስቆም ጉዳይ ከሞስኮ ጋር እየመከረ ባለበት ወቅት ነው።
ፕሬዝደንት በዶናልድ ትራምፕ በዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ላይ እያደረጉ ያሉትን ትችትም አጠናከረው ቀጥለዋል። አውሮፓውያን አሜሪካ በዩክሬን ጦርነት እያሳየች ያለውን የፖሊሲ ለውጥ ለማስተካከል እየተሯሯጡ ሲሆን የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በትናንትናው እለት በኃይትሀውስ ተገናኝተው መክረዋል።
በአውሮፓውያን የሚደገፈው በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በ93 ድምጽ ጸድቋል። "ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው አጠቃላይ ጦርነት ለሶስት አመታት መቀጠሉን በስጋት እንደሚያየውና ለዩክሬን ብቻ ሳይሆን ለቀጣናዎች ብሎም ለአለም መረጋጋት ለረጅም ጊዜ የሚቆይ አሉታዊ ተጽጽኖ ይኖረዋል" ሲል የጠቀሰው የውሳኔ ሀሳቡ የዩክሬኑ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥሪ አቅርቧል።
የውሳኔ ሀሳቡ ሩሲያ "ያለምንም ቅድመ ሁኔታና በፍጥነት ኃይሏን አለምአቀፍ እውቅና ካለው የዩክሬን ግዛት እንድታስወጣ" ጠይቋል።
አሜሪካ ሩሲያን እንደወራሪ የማይፈርጅና ለዩክሬን የግዛት አንድነት እውቅና የማይሰጥ ተፎካካሪ የውሳኔ ሀሳብ አቅርባለች። በአሜሪካ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ጦርነቱ በፍጥነት እንዲቆምና በዩክሬንና ሩሲያ መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር የሚጠይቅ ነው።
አውሮፓውያን ስብሰባውን ለማዘግየት ያደረጉት ጥረት አለመሳካቷን ተከትሎ ሩሲያን ጨምሮ በ10 ድምጽ ድጋፍና በአምስት ተአቅቦ ድምጽ የውሳኔ ሀሳቡ ጸድቋል። በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ የተካተቱ ጠንካራ ቃላቶችን ለመጨመር የነበረው ሀሳብ ሩሲያ በመቃወሟ ምክንያት በጸጥታው ምክርቤት ተቀባይነት አላገኘም።