ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል
የሪፕብሊካን እጩ የሆኑት እና የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ዳግም ወደ ስልጣን ተመልሰዋል።
የምርጫ ውጤቱ ይፋ ከመደረጉ ቀደም ብሎ ትራምፕ በዌስት ፓልም ቢች ካውንቲ የስብሰባ ማዕከል ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ማሸነፋቸውን አውጀዋል።
በቃልኪዳን እና ምስጋና በታጀበው ንግግራቸው ኢኮኖሚ፣ መከላከያ እና የስደተኞች ጉዳይን ያነሱ ሲሆን፤ ለበለቤታቸው ሜላኒያ እና ለቤተሰቦቻው እንዲሁም ለቢሊየነሩ ኤለን መስክና በምርጫው ከጎናቸው የነበሩ ሰዎችን በሙሉ አመስግነዋል።
ትራምፕ በንግግራቸው ያነሱ ዋና ዋና ነጥቦችን ከታች ባለው ምስል ይመልከቱ፤