ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ
ዶናልድ ትራምፕ እስካሁን ባለው የምርጫ ውጤት 277 ድምጽ በማግኘት ተቀናቃኛቸው ካማላ ሀሪስን አሸንፈዋል
ዶናልድ ትራምፕ ጥር ወር ላይ በይፋ ስልጣን ከተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይረከባሉ
ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን አሸንፈዋል፡፡
ምርጫውን ለማሸነፍ እጩዎች ቢንስ 270 እና ከዛ በላይ የመራጭ ወኪሎችን ድምጽ ማግኘት ግዴታ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ይህን አሳክተዋል፡፡
ይህንን ተከትሎም ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን መመረጣቸው ተገልጿል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ያሸነፉት 19 የመራጮች ድምጽ ያለው ፔንሲልቫኒያ ግዛትን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ምርጫውን ለማሸነፍ በዝቅተኛነት የተቀመጠውን 277 ድምጽ አስገኝቶላቸዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካንን ከፈረንጆቹ 2016 እስከ 2020 ድረስ በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉ ሲሆን ከአራት ዓመት በፊት በተካሄደ ተመሳሳይ ምርጫ በጆ ባይደን ተሸንፈው ስልጣን አስረክበው ነበር፡፡
በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ምርጫ ታሪክ ዶናልድ ትራምፕ በተከታታይ መምራት ያልቻሉ እና ዳግም በመወዳደር ፕሬዝዳንት መሆን የቻሉ ሁለተኛው ፕሬዝዳንት ሆነዋል ሲል ኤፒ ዘግቧል፡፡
ምክትላቸው ጄቫንስ ደግሞ የአሜሪካ 50ኛው ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በተለይም ወንዶች እና የኢኮኖሚ ጉዳይ ያሳሰባቸው አሜሪካዊያንን ትኩረት ስበዋል ተብሏል፡፡