ለትራምፕ ድምጻቸውን የሰጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የትኞቹ ናቸው
ትራምፕ የላቲኖ አሜሪካን ፣ የጥቁሮችን እና ኢኮኖሚን ቀዳሚ ጉዳያቸው ያደረጉ ዜጎችን በርካታ ድምጽ አግኝተዋል
ትራምፕ በፍሎሪዳ ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር በምርጫው ማሸነፋቸውን አውጀዋል
ለትራምፕ ድምጻቸውን የሰጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የትኞቹ ናቸው
ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ 47ኛ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው መመረጣቸውን የአሜሪካ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ትራምፕ በ277 ድምጽ በሰፊ ውጤት ነው ያሸነፉት።
ትራምፕ በዛሬው እለት ጠዋት በዌስት ፓልም ቢች ካውንቲ የስብሰባው ማዕከል የተገኙ ደጋፊዎቻቸው ባረሙት ንግግር "ድንቅ ድል አደርገናል" ሲሉ ምርጫውን ማሸነፋቸውን አውጀዋል።
በፍሎሪዳ በዌስት ፓልም ቢች ከደጋፊዎቻቸው ጋር በነበራቸው ቆይታ 47ተኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን መመረጣቸውን አውጀዋል፡፡
ቀጣዮቹን አራት አመታት የድንበር ጥበቃዎችን በማጠናከር እና ኢኮኖሚውን በማሻሻል ትኩረት እንደሚያደርጉ የተናገሩት ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውን እና መራጮችን አመስግነዋል፡፡
የሚጠብቀን ስራ ከባድ እና አድካሚ ነው ያሉት የሪፐብሊካኑ እጩ በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰቱ ጦርነቶችን እንደሚያስቆሙ የገቡትን ቃልም ከመፈጸም የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለ ተናግረዋል
በዘንድሮ ምርጫ ሁሉቱም እጩዎች የመራጮችን ድምጽ አገኝበታለሁ ያሏቸውን ከኢኮኖሚ እስከ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ የድንበር ጥበቃ እና ህገወጥ ስደተኝነት እንዲሁም በሌሎች ፖሊሲያዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን አቅርበዋል፡፡
ትራምፕ ምርጫውን ማሸነፋቸውን አወጁ
ለትራምፕ ከፍተኛ ድምጽ የሰጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የትኞቹ ናቸው
ሀገሪቱ ወደ በአሉታዊ አቅጣጫ እየተጓዘች ነው ብለው የሚያምኑ መራጮች (61%) ያህሉ ለትራምፕ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል፡፡
ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች አስፈላጊ ናቸው ያሉ መራጮች ደግሞ ከ79-80 በመቶ ትራምፕን መርጠዋል፡፡
ሴቶችን በተመለከተ ሃሪስ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚኖራቸው ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም ትራምፕ 51 በመቶ የሴቶችን ደምጽ ስለማግኝታቸው ተሰምቷል፡፡
ከቆዳ ቀለም ጋር በተያያዘ ደግሞ የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ላቲኖ እና ጥቁር አሜሪካውያንን በማሳመን ደረጃ የተሳካ ስራ መስራቱን ሮይተርስ አስነብቧል፡፡
በኖርዝ ካሮላይና ግዛት ብቻ 12 በመቶ የጥቁር አሜሪካውያንን ድጋፍ ሲያገኙ ወንድ ጥቁር መራጮች ከአራት አመት በፊት ከነበራቸው ድጋፍ በአምስት በመቶ ብልጫ እንዳለው ተነግሯል፡
በ2020 አራት በመቶ ብቻ የላቲኖ አሜሪካን ድምጽ ባገኙበት የኔቫዳ ግዛት በዘንድሮው አመት 11 በመቶ ድምጽ መያዝ ችለዋል፡፡
በእድሜ ደረጃ ትራምፕ ከ18 እስከ 45 አመት እድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ አሜሪካውያን ዘንድ ተመራጭ ናቸው፡፡
በአንጻሩ ሃሪስ በወጣት እድሜ እና በጎልማሳ እድሜ ላይ በሚገኙ ሴቶች እንደሁም ከ45 አመት በላይ በሚገኙ ሁለቱም ጾታዎች የተሻለ ድጋፍ አግኝተዋል፡፡