ትራምፕ ማሸነፋቸውን ያወጁት በዘሬው እለት ጠዋት በዌስት ፓልም ቢች ካውንቲ የስብሰባ ማዕከል ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው
ትራምፕ ምርጫውን ማሸነፋቸውን አወጁ
የሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ የ2024ቱን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን የአሜሪካ ሚዲያዎች ዘገቡ
ትራምፕ ማሸነፋቸውን ያወጁት በዘሬው እለት ጠዋት በዌስት ፓልም ቢች ካውንቲ የስብሰባ ማዕከል ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።
የተቀናቃኛቸው ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሀሪስ የማሸነፍ ጉዞ፣ የትራምፕ የማሸነፍ ግምት በመስፋቱ 270 ድምጽ የማግኘት እድላቸው ጠቧል።
ዋነኞቹ የአሜሪካ ሚዲያዎች ኤፒ እና ሲኤንኤን ጨምሮ ቆጠራው ገና ያልተጠናቀቀ መሆኑን ቢገልጹም ትራምፕ ግን ማሸነፋቸውን አውጀዋል።
"ማንም አይቻልም ያለውን መሰናክል አልፈናል" ብለዋል ትራምፕ። "የማይታመን የፖለቲካ ድል ማግኘታችን አሁን ግልጽ ነው።"
ዲሞክራቶች ትራምፕ እንደ ምርጫ 2020 ምርጫው ሳይጠናቀቅ አሸንፌያለሁ ብለው ሊያውጁ ይችላሉ በሚል ስጋታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።