ትራምፕ በ15 ግዛቶች ሲያሸንፋ፣ ሀሪስ ደግሞ በ7 ግዛቶች ድል ቀንቷቸዋል
ጠንካራ ፉክክር ይካሄድባቸዋል የተባሉት ግዛቶች የምርጫ ውጤት በሰአታት ውስጥ የመጠናቀቅ እድሉ አነስተኛ ስለሆነ አሁን አሸናፊውን ለመለየት አሽጋሪ ነው ተብሏል
ጠንካራ ፉክክር የሚደረግባቸው ግዛቶት አሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ሚቺጋን፣ ኔቫዳ፣ ኖርዝ ካሮላይና፤ ዊስኮንሲን እና ፔንስልቬንያ ናቸው
ትራምፕ በ15 ግዛቶች ሲያሸንፋ፣ 7 ሀሪስ ደግሞ በ7 ግዛቶች ድል ቀንቷቸዋል።
በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫ ብርቱ የሚባል ፉክክር እየተካሄደ ሲሆን እስካሁን ትራምፕ 15 ግዛቶችን እና ተቀናቃኛቸው ሀሪስ ደግሞ ሰባት ግዛቶችን ማሸነፋቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ነገርገን ጠንካራ ፉክክር ይካሄድባቸዋል የተባሉት ግዛቶች የምርጫ ውጤት በሰአታት ውስጥ የመጠናቀቅ እድሉ አነስተኛ ስለሆነ አሁን አሸናፊውን ለመለየት አሽጋሪ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
እስካሁን ያለው ውጤት እንደተጠበቀው የእነዚህ ግዛቶችን ድምጽ ወሳኝነት የሚያሳይ ነው።
ግዛቶቹ አሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ሚቺጋን፣ ኔቫዳ፣ ኖርዝ ካሮላይና፤ ዊስኮንሲን እና ፔንስልቬንያ ናቸው።
አሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ሚቺጋን፣ ኔቫዳ፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ፔንስልቬንያ በተከታታይ 1፣ 16፣ 15፣ 6፣ 16 እና 19 ወኪል መራጮች አሏቸው።
የህዝብ አስተያየት እንደሚያሳየው ከሆነ ትራምፕ እና ሀሪስ እስከ ምርጫው እለት ድረስ በግዛቶቹ አንገት ለአንገት ተናንቀዋል።
ብርቱ ፉክክር የሚካሄድባቸው ወይም 'ባትልግራውንድ ስቴትስ' ወይም 'ስዊንግ ስቴትስ' በመባል የሚጠሩት በግዛቶቹ መራጮች እኩል በሚባል ደረጃ ተከፋፍለው ወደ ምርጫ ስለሚያቀኑ ነው።
ሌሎች በርካታ ግዛቶች በተደጋጋሚ ለሪፐብሊካን ወይም ለዲሞክራቶች ድምጽ የሚሰጡ ስለሆነ ሁለቱም ወገኖች ብርቱ ፉክክር በሚካሄድባቸው ግዛቶች ለማሸነፍ ብዙ ጊዜ እና ገንዘብ ኢንቨስት ያደርጋሉ።
እንደ ሲኤንኤን ቴሌቪዥን ዘገባ ከሆነ ትራምፕ ሀሪስን በወኪል መራጮች 211 ለ145 እየመሩ ይገኛሉ። ነገርግን ሁለቱም የሚያሸንፉባቸው እድሎች አላቸው።
ፕሬዝደንት ሆኖ ቤተመንግሥት ለመግዛት እጩዎች 270 የወኪል መራጮች ወይም ከየግዛቱ የተወከሉ መራጮች ድሜጽ ያስፍልጋቸዋል።