ከ1845 በፊት በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዕጩ ለመሆን የንብረት ባለቤት መሆን ግድ ነበር
የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እና ቁጥሮች
ተጠባቂው የ2024ቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በይፋ መከናወን ጀምሯል፡፡
ከ78 ሚሊዮን በላይ መራጮች ከይፋዊ የምርጫ ቀን በፊት ድምጽ ሲሰጡ 160 ሚሊየን ሰዎች ለመምረጥ ተመዝግበዋል፡፡
የአለም ዴሞክራሲ ሂደት ማሳያ ተደርጎ በሚታየው የአሜሪካ ምርጫ የመራጮች ተሳትፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ172 ሀገራት 139ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ከ1972 ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ በአሜሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው (61 በመቶ) መራጭ የተሳተፈው በ1992 ሲሆን በዘንድሮው ምርጫ 244 ሚሊየን ዜጎች ድምጽ መስጠች ቢችሉም የተመዘገቡት 160 ሚሊየን ብቻ ናቸው፡፡
በአሜሪካ ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ዕጩ ሆኖ ለመቅረብ በአሜሪካ ሕገ መንግስት አንቀጽ ሁለት ምዕራፍ 1 መሰረት ሶስት ቅድመ ሁኔታዎች ተቀምጠዋል፡፡
በአሜሪካ የተወለደ ፣ በሀገሪቱ ለ14 አመት የኖረ እና እድሜው ከ35 አመት በላይ እንዲሆን ይጠይቃል፡፡
በ1845 ህጉ በኮንግረስ እስከሚሻሻል ድረስ እጩዎች ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር የቋሚ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ ያስገድድ ነበር፡፡
በአሜሪካ ምርጫ ታሪክ ከፓርቲ ውክልና ውጪ በግሉ ተወዳድሮ ያሸነፈው ጆርጂ ዋሽንግተን ለምርጫ ቅስቀሳ ያገኝውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ደጋዎቹን መጠጥ ለመጋበዝ አውሎታል፡፡
ቪክቶርያ ውድሀል በ1972 ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ዕጩ ሆና የቀረበች የመጀመርያዋ ሴት ነበረች፡፡ ቀጥሎም ሄላሪ ክሊንተን በፓርቲ ከፍተኛ ድጋፍ በማግኝት እጩ ሆነው የቀረቡ ሴት በመባል ይታወቃሉ፡፡
በአሜሪካ ታሪክ ስምንት ፕሬዝዳንቶች በስልጣን ላይ እያሉ ህይወታቸው ሲያልፍ ከዚህ ውስጥ አራቱ በሰው እጅ የተገደሉ ናቸው፡፡