ብርቱ ፉክክር የሚካሄድባቸው ሰባቱ ግዛቶች የ2024ቱን ምርጫ ውጤት ለመወሰን ቁልፍ እንደሆኑ እየተገለጸ ነው
በ2024ቱ የአሜሪካ ምርጫ ብርቱ ፉክክር የሚካሄድባቸው 7 ግዛቶች
በመላው አለም በጉጉት የሚጠበቀው የ2024ቱ የአሜሪካ ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል።
ብርቱ ፉክክር የሚካሄድባቸው ሰባቱ ግዛቶች ሪፐብላካንን ወይም ዲሞክራቶችን ሊመርጡ ስለሚችሉ የ2024ቱን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ለመወሰን ቁልፍ እንደሆኑ እየተገለጸ ነው።
ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሀሪስ እነዚህን ግዛቶች በተጋጋሚ የጎበኙ ሲሆን ሲቢኤስ ኒውስ በሰበሰበው የህዝብ አስተያያት መሰረት እስከምርጫው ድረስ አንገት ለአንገት ተናንቀዋል።
ሲቢኤስ ኒውስ እንደገለጸው ከሆነ ግዛቶቹ አሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ሚቺጋን፣ ኔቫዳ፣ ኖርዝ ካሮላይና፤ ዊስኮንሲን እና ፔንስልቬንያ ናቸው።
አሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ሚቺጋን፣ ኔቫዳ፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ፔንስልቬንያ በተከታታይ 1፣ 16፣ 15፣ 6፣ 16 እና 19 ወኪል መራጮች አሏቸው።
በእነዚህ ግዛቶች ዲሞክራቶች እና ሪፐብሊካኖች እየተፈራረቁ ነው ሲያሸንፉ የቆዩት።
ብርቱ ፉክክር የሚካሄድባቸው ወይም 'ባትልግራውንድ ስቴትስ' ወይም 'ስዊንግ ስቴትስ' በመባል የሚጠሩት በግዛቶቹ መራጮች እኩል በሚባል ደረጃ ተከፋፍለው ወደ ምርጫ ስለሚያቀኑ ነው።
ሌሎች በርካታ ግዛቶች በተደጋጋሚ ለሪፐብሊካን ወይም ለዲሞክራቶች ድምጽ የሚሰጡ ስለሆነ ሁለቱም ወገኖች ብርቱ ፉክክር በሚካሄድባቸው ግዛቶች ለማሸነፍ ብዙ ጊዜ እና ገንዘብ ኢንቨስት ያደርጋሉ።