ስዊድን "አሸባሪዎችን ማስጠለሏን" ካለቆመች ቱርክ የኔቶ መቀላቀል ጥያቄዋን ይሁንታ አትሰጥም-ኢርዶጋን
ሀገራት ወደ ኔቶ ለመቀላለቀል የሁሉም የኔቶ አባል ሀገራት ፖርላማ ማጽደቅ ይኖርባቸዋል
ቱርክ እና ሀንጋሪ የሰዊድንን የኔቶ አባልነት ጥያቄ እስካሁን አላጸደቁም
የቱርክ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ስዊድን በቱርክ ሽብርተኛ ተብለው የተፈረጁትን አካላት ማስጠላሏን ካላቆመች ቱርክ ስዊድን ወደ ኔቶ እንዳትቀላቀል የምታደርገውን ተቃውሞ አታነሳም ብለዋል።
ስዊድን እና ፊንላንድ ለረጅም ጊዜ ይዘውት የነበረውን የገለልተኝነት አቋም በመተው ኔቶን ለመቀላቀል የወሰኑት ሩሲያ ዩክሬን መውሯን ተከትሎ ነበር።
ሀገራት ወደ ኔቶ ለመቀላለቀል የሁሉም የኔቶ አባል ሀገራት ፖርላማ ማጽደቅ ይኖርባቸዋል።
ቱርክ እና ሀንጋሪ የሰዊድንን የኔቶ አባልነት ጥያቄ እስካሁን አላጸደቁም።
ስዊድን በሽብር በፈረጀችው የኩርዲስታን ሰራተኞች ፖርቲ(ፒኬኬ) ደጋፊዎች እና በ2016 መፈንቅለ መንግስት አድራጊዎች ላይ ተጨማሪ እርምጃዎችን መወሰድ እንዳለባት ቱርክ ገልጻለች።
ቱርክ ሁለቱንም ቡድኖች ሽብርተኛ ብላ ፈርዳቸዋለች።
ኤርዶጋን ከካቢኔ ስብሰባ በኋላ በሰሙት ንግግር ቱርክ ስዊድን ሁለቱን ቡድኖች ማስጠለሏን ታቆማለች ብላ ትጠብቃለች።
አሸባሪዎች በዋና ዋና አደባባዮች ሰልፍ እንዲያደርጉ እየፈቀዱ ከቱርክ ጋር ወዳጅነት መመስረት እንደማይቻል ማንኛውም ሰው ማወቅ አለበት ብለዋሎ ኤርዶጋን።
በቅርቡ በስዊድን በተካሄደ ሰልፍ በቱርክ እና ምዕራባውያን አጋሮቿ በሽብርተኝነት የተፈረጀው የፒኬኬ ባንዲራ ተውለብልቧል።
ፕሬዝደንት ኤርዶጋን አቋማችኖ ግልጽ ነው፤ ለመርህ ነው የቆምነው ሲሉም ተናግረዋል።