በፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ተቀናቃኛቸው በጠባብ ልዩነት በመብለጥ በድጋሚ ቱርክን የመምራት እድል አግኝተዋል
በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሸነፉ።
የምርጨውን ውጤት ተከትሎ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ባስተላፉት መልእክት፤ “በምርጫ ድምጽ በመስጠት ዲሞክራሲያዊ ባህላችን እንዲዳብር ያደረጉን ወገኖቻችንን አመሰግናለሁ” ብለዋል።
“ለቀጣይ 5 ዓመታት ቱርክን እንድመራ የሀገሪቱ ህዝብ ኃፊነት ሰጥቶኛል” ያሉት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን፤ “ዲሞክራሲያችንን፣ ልማታችንን እና ግባችንን አሳልፈን ከማሳካት ወደኋላ የሚመልሰን የለም” ሲሉም ገልጸዋል።
“የምርጫው አሸናፊ የቱርክ ህዝብ ነው፤ በቀጣይ ዓመት የሚደረግ አካባቢያዊ ምርጫንም እናሸንፋለን ሲሉም ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ተናግረዋል።
በፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ተቀናቃኛቸው በጠባብ ልዩነት በመብለጥ በድጋሚ ቱርክን የመምራት እድል አግኝተዋል።
እስካሁን በተካሄደ 99.20 በመቶ የድምጽ ቆጠራ ጊዜያዊ ቆጠራ ላለፉት 20 ዓመታት ቱርክን የመሩት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን 52.08 በመቶ እንዲሁም ተቀናቃኛቸው ክሊክዳርጎሉ ደግሞ 47.92 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል
በቱርክ ባለፈው ግንቦት 14 በተካሄደው ምርጫ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን እና ዋና ተቀናቃኛቸው ክሊክዳርጎሉ አብላጫ ድምጽ ማግኘት ባለመቻላቸው ምርጫው በድጋሚ መካሄዱ ይታወሳል።