ፖለቲካ
ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን የሚደገመውን ምርጫ የቱርክ የክፍለ ዘመኑ 'አብሳሪ' እናደርገዋለን አሉ
በቱርክ ምርጫ እጩዎች መንግስት ለመመስረት የሚያስችላቸውን አብላጫ ድምጽ ባለማግኘታቸው ይደገማል
ኤርዶጋን "በሀገራችን ወሳኝ ምርጫ የመጀመሪያውን ፈተና በንጹህ ህሊና አልፈናል" ብለዋል
ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን የግንቦት 28ቱን ምርጫ አስመልክቶ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን "መጪዎቹን ቀናት በተሻለ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንደምንገመግም ተስፋ አደርጋለሁ። በፈጣሪ ፍቃድ ግንቦት 28ን የቱርክ ክፍለ ዘመን አብሳሪ እናደርገዋለን" ብለዋል።
በሀገራችን በጣም ወሳኝ ለሆነው ምርጫ የመጀመሪያውን ፈተና በንጹህ ህሊና አልፈናል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በችግሮች ውስጥ ሳንሸነፍ ጠንክረን ታግለናል ሲሉም አክለዋል።
ለዚህም ምስጋና ያቀረቡት ኤርዶጋን፤ በግንቦት 14 ያገኘነውን ስኬት ድል የምንቀዳጅበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋልም።
"ቱርክ አገልግሎትን ከእኛ ትጠብቃለች፣ ተግባርን ትጠብቃለች፣ሀገራችን ግቦቿን እንድናሳካ እየጠበቀችን ነው'' ብለዋል።
ፕሬዝደንት ጣይብ ኤርዶጋን እሁድ የተደረገውን ምርጫ በ49 በመቶ ድምጽ ቢመሩም መንግስት ለመመስረት የሚያስችላቸውን አብላጫ ድምጽ አላገኙም።
ተቀናቃኛቸው ግንቦት 28 በሚደረገው ሁለተኛ ዙር ምርጫ ፕሬዝዳንቱ የስልጣን ዘመናቸውን ለሦስት አስር ዓመታት እንዳያራዝሙ ለማድረግ ከፍተኛ ትግል ያደርጋሉ ተብሏል።