በቱርኩ ምርጫ 3ኛ ደረጃ የነበረው እጩ ድጋፉን ለፕሬዝደንት ኤርዶጋን ሰጠ
ኦጋን ብቻውን ማሸነፍ እንኳን ባይችል አሸናፊውን መወሰን የሚችል እድል አለው የሚል ትንታኔ ሲሰጥ ነበር
በባለፈው ምርጫ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን 49.5 በመቶ ድምጽ ሲያገኙ ተቀናቃኛቸው ክሊክዳርጎሉ ደግሞ 44.9 በመቶ ድምጽ ማግኘት ችለው ነበር
በቱርክ እየተካሄደ ባለው ምርጫ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ያለው እጩ ለፕሬዝደንት ኤርዶጋን ድጋፉን በመስጠት ዋና ተቀናቃኝ የሆኑት ከማል ክሊክዳርጎሉ የሚደርስባቸውን ፉክክር እንዲጠነክርባቸው አድርጓል።
ከምርጫ ቅስቀሳው በፊት በህዝብ ዘንድ ብዙም የማይታወቀው ሲናን ኦጋን በግንቦት ሁለኛው ሳምንት በተካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ 5.2 በመቶ ድምጽ አግኝቶ ነበር።
ኦጋን ብቻውን ማሸነፍ እንኳን ባይችል አሸናፊውን መወሰን የሚችል እድል አለው የሚል ትንታኔ ሲሰጥ ነበር።
"በሁለተኛው ምርጫ ኤርዶጋንን እንደምንደግፉ ውሳኔ አሳልፌያለሁ" ሲል ኦጋን በአንካራ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
የክሊክ ዳርጎሉ ኔሽን አሊያንስ ፖርቲ "ስለወደፊቱ ያቀደው አላሳመነንም" ነገርግን የኤርዶጋን በሽብርተኝነት ላይ ያላቸው የማያቋርጥ የትግል መርህ ለመደገፍ ምክንያት ሆኖናል ብሏል ኦጋን።
በባለፈው ምርጫ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን 49.5 በመቶ ድምጽ ሲያገኙ ተቀናቃኛቸው ክሊክዳርጎሉ ደግሞ 44.9 በመቶ ድምጽ ማግኘት ችለው ነበር።
በዚህ ምርጫ ከ50በመቶ በላይ ድምጽ ያገኘ እጩ ባለመኖሩ ምርጫው እንዲደገም ተደርጓል።
የ55ቱ ኦጋን በቪክተር ፖርቲ የሚመራው የቀኝ ዘመም ጥምረትን በመወከል ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሬዝደንታዊ ምርጫ ፉክክር ተሳትፏል።
ኦጋን ለሮይተርስ እንደገለጸው ዋነኛ አላማው በዋናነት የኩርዲሽ ፖርቲዎችን ከቱርክ ማስወገድ እና የቱርክ ብሄራዊ አንድነት ማጠናከር መሆኑን ገልጿል።
የኩርዶች ደጋፊ የሆነው ኤችዲፒ ፖርቲ ክሊክዳርጎሉን የደገፈ ሲሆን የኩርዲሽ እስላሚስት ደግሞ ኤርዶጋንን ደግፏል።
የተራዘመው የቱርክ ምርጫ በፈረንጆቹ ግንቦት 28 ይካሄዳል።