ፖለቲካ
ኘሬዝደንት ኤርዶጋን ተቃዋሚዎቻቸውን "የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት" ደጋፊ ናቸው ሲሉ ከሰሱ
ኤርዶጋን ተቃዋሚዎች ሽብርተኞችንም ይደግፋሉ የሚል ክስ አቅርበዋል
በዚህ ምርጫ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን በሁለት አስርት አመታት ውስጥ አይተውት የማያውቁት ፈተና ይገጥማቸዋል እየተባለ ነው
የቱርኩ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ተቃዋሚዎቻቸውን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ደጋፊ ናቸው ሲሉ ከሰዋል።
ኘሬዝደንቱ ይህን ክስ ያቀረቡት በቱርክ ኢስታንቡል ከተማ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ ቁጥር ያለው ደጋፊ ፊት ባደረጉት ንግግር ነው።
ኤርዶጋን ተቃዋሚዎች ሽብርተኞችንም ይደግፋሉ የሚል ክስ አቅርበዋል።
ኘሬዝደንት ኤርዶጋን አንድ ሳምንት በቀረው እና ጠንካራ ፉክክር ይታይበታል በሚባለው ምርጫ በድጋሚ ሀገሪቱን ለመምራት ይወዳደራሉ።
ለፕሬዝደንት ኤርዶጋን ኤኬ ፖርቲ እንደምሽግ በምትታየው በምስራቃዊቷ ኢዙርም ከተማ በተካሄደ ተቃውሞ የዋና ተቃዋሚው የሪፐብሊካን ፒፕልስ ፖርቲ አባል በሆነው የኢስታንቡል ከተማ ከንቲባ ላይ ድንጋይ ተወርውሮበታል።
ከንቲባው ኢማሞግሉ በድንጋይ ውርወራው ዘጠኝ ሰዎች ተጎድተዋል ብለዋል።
በዚህ ምርጫ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን በሁለት አስርት አመታት ውስጥ አይተውት የማያውቁት ፈተና ይገጥማቸዋል እየተባለ ነው።
በቱርኳ ኢስታንቡል ከተማ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ አደባባይ በመውጣት ፕሬዝደንት ኤርዶጋን በድጋሚ እንዲመረጡ ድጋፋቸውን አሳይተዋል።