አውሮፕላኑ በዚህ ዓመት የበረራ ፈቃድ ከተሰጠው ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ለዓለም ገበያ ይቀርባል ተብሏል
ቱርክ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጥ አነስተኛ አውሮፕላን ሰራች።
በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለዓለም በማስተዋወቅ የምትታወቀው ቱርክ አነስተኛ አውሮፕላን ማምረቷን አስታውቃለች።
እንደ አናዶሉ ዘገባ ትሮይ ቲ200 የተሰኘ የታክሲ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አነስተኛ አውሮፕላን የመጨረሻ የሙከራ በረራ አድርጋለች።
በሰሜናዊ ምዕራብ ቱርክ የምትገኘው ቡርሳ ኢንዱስትሪ የተመረረተው ይህ አነስተኛ አውሮፕላን የሙከራ በረራውን አጠናቋል ተብሏል።
አውሮፕላኑ በኡክሳን አቪዬሽን ኩባንያ የተሰራ ሲሆን ላለፉት አራት ዓመታት የምርት እና ሙከራ በረራውን ሲያካሂድ እንደቆየም ተገልጿል።
430 ኪሎ ግራም ክብደት እንዳለው የተገለጸው ይህ አነስተኛ የታክሲ አውሮፕላን በተያዘው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት የበረራ ፈቃድ እንደሚያገኝም ተጠቅሷል።
ከ2024 ጀምሮም በስፋት በማምረት ለዓለም አቀፍ ገበያ እንደሚቀርብ ኩባንያው አስታውቋል።
የታክሲ አገልግሎት ይሰጣል የተባለው ይህ አነስተኛ አውሮፕላን ለግብርና፣ ለአብራሪዎች ስልጠና ቅኝቶችን ለመከወንም ትውላለች ተብሏል።