“ቲ.ኤ.አይ አክሱንጉር” ስድስት አይነት ቦምቦች ታጣቂውና አደገኛው የቱርክ ድሮን
በሰዓት 250 ኪ.ሜትሮችን የሚከንፈው ድሮኑ 6 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር ድረስ ማካለል ይችላል
“ቲ.ኤ.አይ አክሱንጉር” የምድር ላይ ብቻ ሳይሆን የባህር ስር የጠላት ሰርጓጅ መርከቦችን ለይቶ ያወድማል
በሰው አልባ የውጊ አውሮፕላኖች (ድሮን) ስሟ ተደጋግሞ የሚነሳው ቱርክ ወታደራዊ ተቋሞቿን በከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ማዘመኑን ተያይዛዋለች።
የቱርክ የመከላከያ ተቋም ባይካር በዚህ ዘፍር ከቀዳሚዎቹ አንዱ መሆን የቻለ ሲሆን፤ በተቋሙ ከተመረቱ ድሮኖች ውስጥም “ቲ.ኤ.አይ አክሱንጉር” አንዱ ነው።
አደገኛ እና ለማንም አይመለስም የተባለለት ይህ ድሮን በፈረንጆቹ በ2021 የተዋወቀ ሲሆን፤ ውጊያ ላይ ባለው ዘርፈ ብዙ አገልግሎትም አቻ የለውም እየተባለለት ነው።
ድሮኑ በሰማይ ላይ እና በመሬት ላይ ከሚገኙ ኢላማዎች እስከ ባህር ስር ያሉ ኢላማዎችን አነጣጥሮ የማውደም አቅም እንዳለውም ነው የሚነገርለት።
“ቲ.ኤ.አይ አክሱንጉር” (TAI Aksungur) ድሮን ከመሬት በ12 ሺህ ሜትር ከፍታ ላይ በመሆን በሰዓት እስከ 250 ኪሎ ምትር መከነፍ ይችላል።
ድሮኑ በአንድ ጊዜ ተልእኮ እስከ 6 ሺህ 500 ኪሎ ሜትሮች ድረስ ማካለል እንደሚችልም መረጃዎች እንደሚጠቁሙም የሰዋሰው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ገጽ መረጃ ያመለክታል።
“ቲ.ኤ.አይ አክሱንጉር” ድሮን የተለያዩ አይነት ሚሳዔሎችን የሚታጠቅ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ምድር ላይ የሚገኝ ኢላማን ለማውደም የሚውሉት አሉበት።
ድሮኑ በምድር እና በአየር ላይ ካሉ የጠላት ኢላማዎች በተጨማሪም በባህር ስር የሚጓዙ ጠላት ሰርጓጅ መርከቦችንም ለይቶ የሚመቱ ሚሳዔሎችንም ይታጠቃል።
“ቲ.ኤ.አይ አክሱንጉር” ድሮን ከሚሳዔል በተጨማሪም ስድስት አይነት ቦምቦችን የሚታጠቅ ሲሆን፤ እነዚህም
1. MAM: MAM-L እና MAM-C ኢላማቸውን ብቻ ነጥለው የሚያደባዩ ቦንቦች
2. LUMTAS
3. TEBER-81 በሌዘር ጨረር የሚመራ ቦምብ
4. TEBER-82 በሌዘር ጨረር የሚመራ ቦምብ
5. HGK-3 ራስ መር ቦምብ
6. KGK (82) የራሱ የሆነ መብረሪያ ክንፍ ያለው ቦምብ ናቸው።