የቱርክ ባለስልጣናት በዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ወቅት መሳሪያ ከኤአይ ጋር በማገናኘት ጥያቄዎችን ሲመልስ የደረሱበትን ተማሪ አስረዋል
ቱርካዊው ተማሪ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን (ኤአይ) በመጠቀም ሲኮርጅ ተያዘ።
የቱርክ ባለስልጣናት በዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ወቅት መሳሪያ ከአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ(ኤአይ) ጋር በማገናኘት ጥያቄዎችን ሲመልስ የደረሱበትን ተማሪ አስረዋል።
ይህ ተማሪ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት አጠራጣሪ እንቅሰቃሴዎች በማሳየቱ በፓሊስ ሊያዝ እንደቻለ ሮይተርስ ዘግቧል።
በፓሊስ በጊዜያዊነት በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው ተማሪው አሁን ላይ ወደ መደበኛ እስርቤት ተዛውሮ የሚመሰረትበትን ክስ እየጠበቀ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
ተማሪውን ሲረዳ የነበረው ሌላ ሰውም በቁጥጥር ውሏል ተብሏል።
በደቡባዊ ስፓርታ ግዛት ፓሊስ የተለቀቀው ቨዲዮ ተማሪው እንዴት ካሜራን የሸሚዝ ቁልፍ በማስመሰል በጫማው ሶሎ ውስጥ በተደበቀ ራውተር አማካኝነት ከኤአይ ጋር እንዳያያዘው ያሳያል።
ቢዚህ ቪዲዮ የፓሊስ ባልደረባው ሲስተሙ መስራቱን ለማረጋገጥ ጥያቄዎችን ስካን ሲያደርግ እና ከኤአይ ትክክለኛውምን መልስ በጆሮ ማዳመጫ ሲሰማ ይታያል።
ኤኤይ ጥናት እና ምርምር ለሚሰሩ ሳይንቲስቶች መረጃዎችን በመተንተን፣ በመተንበይ እና ውጤቶችን በመገመት እገዛ ይሰጣል። ኤአይ በአጠቃላይ የሰው ልጆችን ህይወት ቀለል ለማድረግ ወሳኝ ሚና ቢጫወትም ያሉት አሉታዊ ተጽዕኖዎችም በቀላሉ የሚታዩ አይደሉም። ሰዎች በራሳቸው እንዳይሰሩ እና ወደ ኩረጃ እንዲገቡ በር መክፈቱ አንደኛው የኤአይ ችግር ሆኗል።