ፕምፖዮ ወደ ኢራን የሚሄደውን የጦር መሳሪያ በመከላከል ላደረገችው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል
ፕምፖዮ ወደ ኢራን የሚሄደውን የጦር መሳሪያ በመከላከል ላደረገችው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ እንደገለጹት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች(ዩኤኢ) ጋር በሊቢያና በየመን ሰላም በሚሰፍንበት ሁኔታ መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትር ፖምፒዮ እንደተናገሩት አሜሪካን ከዩኤኢ ጋር የሚያጣምር ጠንካራ ግንኙነት መመስረቷን ገልጸዋል፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ለማስፈን አሜሪካ ከዩኤኢ ጎን በመሆን እንደምትሰራ የሁለትን ሀገራት ስትራቴጂክ ግንኙነት ለመመስረት በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል፡፡
ፕምፖዮ ወደ ኢራን የሚሄደውን የጦር መሳሪያ በመከላከል ላደረገችው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የዩኤኢ የውጭ ጉዳይና አለምአቀፍ ግንኙነት ሚኒስትር ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አልነህያን በበኩላቸው ዩኤኢና አሜሪካ ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንደሚመሰርቱ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ በንግግራቸው እየጠነከረ የመጣውንና አሁንም አደጋ የሆነውን አክራሪነትና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ጥረት መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አልነህያን ኢራን የኑክሊየር መሳሪያ እንዳታገኝ መከላከል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡