አሜሪካ የሰብአዊ ቀውስ ላጋጠማቸው ሀገራት የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓን አስታውቃለች
አሜሪካ የሰብአዊ ቀውስ ላጋጠማቸው ሀገራት የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓን አስታውቃለች
አሜሪካ እንዳስታወቀችው ከ720 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሶሪያ የተለፈጠረው ቀውስ ለስብአዊ እርዳታ የሚውል ድጋፍ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡
አሜሪካ ከሶሪያ በተጨማሪም ፣በአፍሪካ ለሳህል ክልል የ152 ሚሊዮን ዶላርና ለደቡብ ሱዳን ደግሞ የ108 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስቴፈን ቤጉን ይህን ያስታወቁት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉዳይ ላይ በተጓዳኝ ባደረጉት ስብሰባ ነው፡፡
በተመሳሳይ ስብሰባ ዩኤስአይዲ ተጠባባቂ አስተዳዳሪ ጆን ባርሳ እንዳስታወቁት በደቡብ ሱዳን ለተፈጠረው የስብአዊ ቀውስም የ108 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
ባርሳ እንደተናገሩት ዋሽንግተን ለኒጀር፣ለማሊ፣ለቡርኪናፋሶና ለማዉሪታኒያ የ152 ሚሊዮን ዶላር የሰብአዊ እርዳታ ትሰጣለች፡፡ እርዳታው በቀጣናው ባለው ግጭት ምክንያት የሚፈጠረውን የሰዎች መፈናቀልንና የምግብ ዋስትና ችግርን ለመቅረፍ ነው ብለዋል፡፡
ቤጉን እንደገለጹት ለሶሪያ የተሰጠው ተጨማሪ እርዳታ ቀውሱ ከተፈጠረ ጀምሮ የአሜሪካን እርዳታ ከ12ቢሊዮን ዶላር በላይ አድርሶታል፡፡
የሶሪያው መሪ በሸር አላሳድ በፈርንጆቹ 2011 በተቃዋሚዎች ላይ ባደረሰው ድብደባ ሀገሪቱን ወደ እርእበእርስ ጦርነት እንድትገባ ያደረገ ሲሆን ኢራንና ሩሲያ መንግስትን ሲረዱ አሜሪካ ደግሞ ተቃዋሚዎችን ስትደግፍ ቆይታለች፡፡
በሀምሌ አሳም ምንም እርዳታ እንዳያገኝ አሜሪካ ማእቀብ ጥላ ነበር፡፡ የሶሪያ ባለስልጣናት በሀገሪቱ ለተከሰተው የዜጎች እንግልት ምእራባውያንን ወቅሳለች፤ የሀገሪቱ ገንዘብ መውደቅ ዜጎች ምግብና መሰረታዊ ፍላጎ ቶችን ለማግኘት እንዲታገሉ አድርጓቸዋል፡፡
አሜሪካ በበኩሏ ማእቀብ የጣለችው ዜጎችን ለመጉዳት አለመሆኑን ትገልጻለች፡፡