በአበረታች መድሃኒት ምክንያት ሁለት የኬንያ አትሌቶች ከኦሎምፒክ ቡድን ውጭ ሆኑ
የ1,500 ሜትር የዓለም ሻምፒዮኑ ቲሞ ቼሩዮትን በኬንያ የኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ ተካቷል
ኬንያ ከአበረታች መድሃኒትን ጋር ተያይዞ የሚነሱባትን ትችቶችን ለማስወገድ እየሰራች መሆኑን አስታውቃለች
ኬንያ አትሌቶቿ ላይ በተደረገ ምርመራ አበረታች መድሃኒት ተጠቅሟል የተባሉት ሁለት አትሌቶቿ ከኦሎምፒክ ብሄራዊ ቡዱን ውጭ ማደረጓ ተሰምቷል።
ይህ ተከትሎም ኬንያ የ 1,500 ሜትር የዓለም ሻምፒዮኑ ቲሞ ቼሩዮትን በቡድኑ ውስጥ እንዲካተት አድርጋለች።
ከዚህም በተጨማሪ ኬንያ የዓለም እና የኦሎምፒክ የመሰናክል ሻምፒዮኑ ኮንሴስስ ኪፕሩቶ በቡድኗ ውስጥ ይካተት ወይስ አይካተት ለሚለው ውሳኔ ትሰጣለች ተብሎ ይጠበቃል።
ኪፕሩቶ ባለፈው ወር ባደረገው የአቋም መለክያ ውድድር ዝቅተኛ አቋም በማሳየቱ ከሁለት ዙር በኋላ ከውድድሩ ውጭ መደረጉ የሚታወስ ነው። በተጨማሪም ባለፈው ዓመት በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ በዋስ መለቀቁም አይዘነጋም።
የኬንያ ብሄራዊ ቡዱን ኃለፊዎች በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ እንደሚመክሩም ነው ሮይተርስ የዘገበው።
ቼሩዮት በ2020 የቶኪዮ ኦሎምፒክ በ 1,500 ሜትር ለወርቅ ይፎካከረራሉ ተብለው ከሚጠበቁ አትሌቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነም ይነገርለታል።
አትሌቱ በዚህ ዓመት ብቻ በርቀቱ ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ ከመቻሉ በስቶክሆልም እና ሞናኮ ባደረጋቸው የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች አሸናፊ መሆን ችሏል።
ቼሩዮት በአበረታች መድሃኒት ምርምራ ምክንያት ከቡዱኑ ውጭ የሆነውና በአቋም መለክያ ውድድሩ በርቀቱ ሁለተኛ በመውጣት በርካቶችን ያስገረመው የ18 ዓመቱ አትሌት ካማር ኢትያንግን የሚተካ ይሆናል።
የኦሎምፒክ ቡዱኑ ኃላፊ ባርናባ ኮሪር“ ኢትያንግ ከቡዱኑ መቀነሱ እጅግ የሚያሳዝን ነው” ብሏል፤ ስለሆነው ነገር ከአትሌቱ ጋር ተነጋግረው መግባባት ላይ መድረሳቸውንም አንስተዋል።
ኬንያ አትሌቶቿ ላይ አከበረታች መድሃኒትን መጠቀም ጋር ተያይዞ የሚነሱባትን ቅሌቶች ለማስወገድ በርካታ ስራዎች በመስራት ላይ ያለች ሀገር ናት።