በኮረና ቫይረስ ምክንያት የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክን መሰረዝ አያስፈልግም- የአለም ጤና ድርጅት
በኮረና ቫይረስ ምክንያት የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክን መሰረዝ አያስፈልግም- የአለም ጤና ድርጅት
የአለም ጤና ድርጅት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክን መሰረዝ ወይንም የውድድር ቦታውን መቀየር እንደማያስፈልግ መግለጹን የአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቲ አስተባበሪ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የድርጅቱ ከፍተኛ የአስቸኳይ ጊዜ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ማይክ ርያን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ከአደጋ ዜሮ የሆነ የብዙሀን ስብስብ የለም”፤ ስለሆነም አዘጋጆቹና የአካባቢው የጤና ባለሙያዎች ችግር ሲያጋጥም መፍትሄ ለመስጠት መዘጋጀት አለባቸው ብለዋል፡፡
የ17 ቀናት ቆይታ የሚኖረው የጃፓን ኦሎምፒክ ሐምሌ 17 ይደመራል ተብሏል፡፡
በተለየ መግለጫ ጃፓን በቫይረሱ ምክንያት አንድ ዶክተርና የታክሲ ሹፌር ከሞቱ በኋላ የቫይረሱን መስፋፋት ለመግታት ምርመራ አጠናክራ መቀጠሏን አስታውቃለች፡፡
እየተስፋፋ ያለውና መነሻውን በቻይናዋ ውሀን ከተማ ያደረገው የኮሮና ቫይረስ በቻይና ሊካሄዱ የነበሩትን የ2020 ኦሎምፒክ የጨዋታ የማጣሪያዎችን፤ የቦክስና የባድሜንተን ጨዋታዎች እንዲሰረዙ አድርጓል፡፡
የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ዋና ስራ አስፈፃሚ በጥር መጨረሻ ቫይረሱ ምናልባት ውድድሩ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል በሚል በጣም ተጨንቀው የነበሩ ቢሆንም፣ በሚቀጥለው ቀን ውድድሩ በተያዘለት ቀን እንደሚካሄድ ቃል ገብተዋል፡፡
እካሁን ድረስ በኮሮና ቫይረስ 1,490 በላይ የሞቱ ሲሆን ከ60,000 በላይ ሰዎች ደግሞ በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡