በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የተራዘመው የቶክዮ 2020 የኦሎምፒክ በመጪው ሐምሌ 23 ይጀመራል
ቶኪዮ ለ18ሺ የኦሎምፒክ ሠራተኞች ክትባት ልትሰጥ መሆኗን ገልጻለች፡፡ ከመጪው ሳምንት ጀምሮ ዳኞች እና ፈቃደኛ ሠራተኞችን ጨምሮ ወደ 18ሺ ገደማ ለሚሆኑ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ሠራተኞች ክትባቱ እንደሚሰጥም አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡
ይህ እርምጃ የኦሎምፒክ ውድድሩ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንዲከናወን የሚያደርጉትን ጥረት አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡
የኦሎምፒክ ውድድሮች ሊጀመሩ የቀራቸው የስድስት ሳምንታት ጊዜ ብቻ ቢሆንም ፤ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ዝግጅቱ የኮሮናቫይረስ በሽታን ሊያሰራጭ ይችላል በሚል ስጋት ከፍተኛ የሆነ የውስጥ ተቃውሞ በማስተናገድ ላይ ናቸው፡፡
የሕዝብ አስተያየት መስጫ ጣቢያዎች ሪፖርቶች የሚመላክቱትም ጃፓናውያን ውድድሩ በዚህ ዓመት መካሄድ እንደሌለባት ወይም ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍን እንደሚደግፉ አሳይተዋል ፡፡
የጃፓን የክትባት መርሃ ግብር ቀስ ብሎ የጀመረ ቢሆንም ፤ አሁን በፍጥነት በሚወሰድበት ጊዜ ግን ከአራት በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ ሙሉ ክትባት ማግኘቱ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
የቶኪዮ 2020 ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሴይኮ ሃሺሞቶ “ክትባቶቹ ሠራተኞቹን ውድድሮች በሚኖሩበት ወቅት ስራቸው በነፃነት እንዲሰሩ ያስችላቸወዋል” የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል ፡፡
ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ሴይኮ ሃሺሞቶ ክትባቱ በዋናነት “ከአትሌቶቹ ጋር በተደጋጋሚ የሚገናኙ” ሰው ላይ ያነጣጠረ ነው ማለታችንም ነው ሲ.ጂ.ቲ.ኤን አፍሪካ የዘገበው፡፡
ዳኞች ፣ የኦሎምፒክ መንደር ሰራተኞች ፣ ሰራተኞች እና ተቋራጮች ፣ የአውሮፕላን ማረፊያ ሰራተኞች ፣ የዶፒንግ ምርመራ ባለሥልጣናት ፣ የብሔራዊ ኦሊምፒክ እና ፓራሊምፒክ ኮሚቴዎች ረዳቶች ክትባቱ በዋናነት የሚመለከታቸው ሰራተኞች ናቸውም ብለዋል ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ፡፡
ከ 70ሺ በላይ ፈቃደኛ ሠራተኞች መካከል ከአትሌቶች ጋር መደበኛ የጠበቀ ግንኙነት ይኖራቸዋል ተብለው የተለዩ የተወሰኑ ሰራተኞች እንደሚያካትትም ነው ሴይኮ ሃሺሞቶ የገለፁት፡፡
ክትባቱ በፈረንጆቹ ሰኔ 18 ይጀምራል ያሉት ሀሺሞቶ ውድድሩ ከመከፈቱ በፊት ሁለተኛ ዙር ክትባት እንደሚሰጥም ገልፀዋል፡፡ የባህር ማዶ ተሳታፊዎችን ቁጥር እንዲቀንስ መደረጉ እና ቀደም ሲል ክትባቱን የወሰዱትን ጨምሮ አትሌቶችን በየቀኑ የኮቪድ ምርምራ የሚያካሂዱ መሆቸውንም ጭምር፡፡፡
ቶኪዮን ጨምሮ የጃፓን የተወሰኑ ክፍሎች በአሁኑ ወቅት ሰኔ 20 ቀን የሚያበቃ የቫይረስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ እንደሚገኙና የኢንፌክሽን ቁጥሮች በመቀነስ ላይ መሆናቸው መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
የቶክዮ 2020 የኦሎምፒክ ውድድሮች በመጪው ሐምሌ 23 የሚጀምር ይሆናል፡፡