ቻይና “አሜሪካ 10 ሺህ በላይ የሳይበር ጥቃት ፈጽማብኛለች” አለች
የአሜሪካ መረጃ ጠላፊዎች 140 ጊጋ ባይት ወሳኝ መረጃ እንደዘረፏትም ቻይና አስታውቃለች
ቻይና የተፈፀመባት የመረጃ ጠለፋ በአሜሪካው ብሄራዊ ደህንነት ተቋም የተመራ ነው ብላለች
የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ተቋም በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከ10 ሺህ በላይ የሳይበር ጥቃቶቸን እንደፈጸመባት ቻይና ገለጸች።
በአሜሪካ የሳይበር ጥቃቶችም 140 ጊጋ ባይት ጠቃሚ መረጃዎች መሰረቃቸው እንዳልቀረ የቻይና ብሄራዊ የኮምፒውተር ቫይረስ ግብረ መልስ ኃይል እና ኪሆ የተባለው የኢንተርኔት ደህንነት ተቋም ባጋራ ባካሄዱት ምርመራ አስታውቀዋል።
ተቋማቱ ምርመራውን ማካሄድ የጀመሩት የቻይና ሰሜናዊ የፖሊ ቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር ላይ የሳይበር ጥቃት እንደተፈፀመበት ማስታወቁን ተከትሎ ነው።
ተቋማቱ ጥቃቱን የፈፀመውን ኔትዎርክት ዱካ ተከትለው ባደረጉት ምርመራም ጠላፊው በአሜሪካው ብሄራዊ ደህንነት ተቋም አካል በሆነው ትሮይድ አክሰስ ኦፕሬሽን ቢሮ እንደተፈጸመ ደርሰንበታል ብለዋል።
በዩኒቨርሲቲ ላይ በተፈፀመው የሳይበር ጥቃት በቀጥታ 13 ሰዎች መሳተፋቸው እና የመረጃ ጠላፊዎ የዩኒቨርሲቲዉን የመረጃ ደህንነት መጠበቂያ (ፋየርዎል) ለማለፍ ከ41 በላይ መሳሪያዎችን መጠቀማቸው ተነግሯል።
ጠላፊዎቹ ማንነታቸውን ለመሸፈን ኢራን፣ ደቡብ ኮሪ እና ጃፓንን ጨምሮ በ17 ሀገራት አይ.ፒ እቀያየሩ ሲጠቀሙ ነበርም ብሏል ተቋማቱ ባወጡት መረጃ።
ምርመራውያን ያካሄዱት ተቋማት ወደፊት የአሜሪካ የመረጃ ጠለፋ እና የስለላ ዘዴቆች እና መሰሳሪያዎችን ዝርዝር ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምርመራ ውጤቱን ተከትሎ ምለሽ ሰጠ ሲሆን፤ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ፤ ቻይና ኢንዲህ አይነት ተጋባራትን በጽኑ ታወግዛለች ብለዋል።
አሜሪካ ከሳይበር ጥቃት ተግበሯ ልትታቀብ ይገባል ያሉት ቃል አቀባዩ፤ ቻይና የኔትዎርክ ደህንነትን ለማስጠበቅ ከዓለም አቀፉ ማህበረስበ ጋር ትሰራለች ሲሉም ተናግረዋል።