የአሜሪካ ኤርፖርቶች በአንድ ቀን ብቻ ሶስት ሚሊዮን መንገደኞችን አስተናገዱ
ያሳለፍነው አርብ ዕለት በታሪክ ብዙ መንገደኞች የተስተናገዱበት ዕለት ሆኖ ተመዝግቧል
የአሜሪካ አቪዬሽን ባለስልጣን በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ውስጥ 271 ሚሊዮን መንገደኞችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል
የአሜሪካ ኤርፖርቶች በአንድ ቀን ብቻ ሶስት ሚሊዮን መንገደኞችን አስተናገዱ፡፡
በአሜሪካ የክረምት ወራት የሚጀመርበት ወቅት መድረሱን ተከትሎ አየር መንገዶች በመንገደኞች ብዛት እየተጥለቀለቁ ይገኛሉ፡፡
ያሳለፍነው አርብ ዕለትም ብቻ የአሜሪካ ኤርፖርቶች 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን መንገደኞችን እንዳስተናገዱ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደ ኒዮርክ አይነት ብዙ በረራ የሚደረግባቸው ከተሞች በአየር ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች እጥረት ምክንያት በረራዎችን ሰርዘዋል ተብሏል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ በአንድ ቀን በረራ ያደረጉ መንገደኞች ቁጥር በታሪክ ከፍተኛው ዕለት ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን የመንገደኞች ቁጥር እየጨመረ እንደሚሄድ ይጠበቃልም ተብሏል፡፡
የናይጀሪያ አየር መንገድ መንገደኞችን የተሳሳተ ኤርፖርት ማራገፉ ተገለጸ
ከፈረንጆቹ ሰኔ 1 ጀምሮ እስከ ነሀሴ ወር ድረስ ባሉት ዘጠና ቀናት ውስጥ 271 ሚሊዮን መንገደኞች በረራ እንደሚያደርጉ የሀገሪቱ አቪዬሽን ባለ ስልጣን ትንበያ ያስረዳል፡፡
የአሜሪካ አየር መንገዶች በቀጣዮቹ የክረምት ወራት በቀን 26 ሺህ በረራዎችን ለማድረግ እቅድ እንዳስቀመጡም ተገልጿል፡፡
አሜሪካ ባሳለፍነው ዓመት ክረምት ወራት ውስጥ 255 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተናገዱ ሲሆን የዘንድሮው መንገደኞች ቁጥር በ10 በመቶ እንደሚጨምር ይጠበቃል፡፡
የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ከኮሮና ቫይረስ በፊት ወደ ነበረበት አቋም ሙሉ ለሙሉ እንደተመለሰ ሲገለጽ ቀጣዮቹ ወራት በአውሮፓ፣ አሜሪካ እና ሌሎች አህጉራት መንገደኞች አብዝተው የሚንቀሳቀሱበት ወቅት ነው፡፡