አሜሪካ የዓለም ዋነኛ የጦርነት ፈጣሪ ከመሆን እንድትታቀብ ቻይና አስጠነቀቀች
አሜሪካ ከ1991 ወዲህ 251 ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቶችን በማሄድ ጦርነቶች እንዲከሰቱ ማድረጓን የሚያሳይ መረጃ ወጥቷል
አሜሪካ እና ቻይና በታይዋን ጉዳይ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል
አሜሪካ የዓለም ዋነኛ የጦርነት ፈጣሪ ከመሆን ልትታቀብ እንደሚገባ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌቢን፤ አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ቤንጃሚን ኖርቶን የሀገሪቱን ኮንግረስ የጥናት አገልግሎት መረጃን ዋቢ በማድረግ ባወጣው ጽሁፍ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።
ጋዜጠኛው ቤንጃሚን ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት አሜሪካ ከፈረንጆቹ 1991 ወዲህ 251 ወታደራዊ ጣልቃ ገብተኖችን በማሄድ ጦርነቶች እንዲከሰቱ አድርጋለች ብሏል።
እንዲሁም ከፈረንጆቹ 1798 ወዲህ ደግሞ 469 ወታደታዊ ጣልቃ ገብነቶችን መካሄዷን አመላክቷል።
ቃል አቀባይ ዋንግ ዌቢን በዚህ መረጃ ላይ በሰጡት አስተያየት፤ አሜሪካ የምታሂካዳው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቶች በህጎች ላይ የተመሰረተ አለም አቀፍ ስርዓት እንደምታከብር ደጋግማ ብትናገርም፤ ኮንግረሱ የለቀቀው መረጃ የአሜሪካ የጦርነት ፈጣሪነትን ከፍተኛ ደረጃ ያንፀባርቃል ማለታቸውን ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።
አሜሪካ ካላት ከ240 በላይ እድሜ ውስጥ ያለ ጦርነት ያሳለፈችው 16 ዓመታትን ብቻ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፤ ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋለ እንኳ አሜሪካ ሰባት ያክል ወታደራዊ ዘመቻዎች አካሂዳለች ብለዋል።
በአሜሪካ ጦር በተደጋጋሚ ኢለማ የሚደረጉ ውስጥም በምድር ላይ የሚገኙትን አብዛኛዎቹን ሀገራት እንደሚያካትቱ ያስታወቁ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ላቲን አሜሪካ፣ ካሪቢያን እና አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ይገኙበታል ሲሉም አሰታውቀዋል።
አሜሪካ በህግ እና በስርዓት ስም ራሷን እንደ ተከላካይ ከመመልከት ይልቅ በጦርነት መሰል ባህሪዋን እና በሌሎች የውስጥ ጉዳዮች ላይ የማያቋርጥ ጣልቃ ገብነቷን ማጤን አለባት ሲሉም አሳስበዋል።
አሜሪካ እና ቻይና በታይዋን ጉዳይ ከሰሞኑ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።
የአሜሪው ፕሬዝዳንት ጀ ባይደን በትናንትናው እለት ቻይና ታይዋንን ከወረረች ጦራቸው ወደ ስፍራው በማቅናት ታይዋንን ይከላከላል ማለታቸው ይታወሳል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ታይዋንን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት ቻይናን ያስቆጣ ሲሆን፤ የጆ ባይደን አስተያየት ዋሽንግተን በታይዋን ላይ ያላትን “ፖሊሲ በእጅጉ የሚጥስ ነው” ብላለች።