በአሜሪካ የሚደገፈው የአረብ-እስራኤል ጥምረት ኢራን ከሩሲያ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት እንድትመሰርት ገፋፍቷታል ተብሏል
የአሜሪካን የኢኮኖሚ ማእቀብ ለመቋቋም ጥረት እያደረገች ያለችው ኢራን በሩሲያ እና በቻይና የሚመራው የሴንትራል እሲያ የጸጥታ አካል ቋሚ አባል ለመሆን ቀርባለች፡፡
ባለፈው ሃሙስ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚርአብዶላሂያን ስብሰባውን በዚህ ሳምንት ያካሄደውን የሻንጋይ ኮኦፐሬሽን ድርጅት(ኤስሲኦ) ለመቀለቀል የሚያስችል መግባባቢያ ሰነድ መፈረማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በፈረንቹ 2001 የተቋቋመው በሩሲያ እና ቻይና የነበረ ሲሆን ከተመሰረተ ከአራት አመት በኋላ ህንድ እና ፓኪስታንን አካቷል፤ ይህም በቀጣናው ያለውን የምእራባውያን ጫና ለመቋቋም አላማ ያደረገ ነበር፡፡
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢንስታግራም ገጻቸው እንደጻፉት ኢራን የኤስሲኦ ሙሉ አባል ለመሆን በመፈረም፣ ኢራን የኢኮኖሚ፤የንግድ እና የኢነርጅ ትብብር የምታደርግበት አዲስ ምእራፍ ውስጥ ገብታለች ሲሉ ጽፈዋል፡፡
የኢራን ፕሬዝደንት ኢብራሂም ሬኢሲ በኡዝቤክስታን የተካሄውን የተካፈሉ ሲሆን በወቅቱም ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር ተገናኝተው የነበሩ መሆኑን የኢራን ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡
አውዛጋቢ በሆነው የኢራን የኑክለር ጉዳይ ምእራባውያን የጣሉባትን መእቀብ የምትቋቋምበትን መንገድ የኤስሲኦ አባልት እንዲረዷት መጠየቋን ተከትሎ ነበር ወደ ቡድኑ እንድትገባ የተፈቀደላት፡፡
ያእደገ የመጣው ማእቀብ እና በአሜሪካ የሚደገፈው የአረብ-እስራኤል ጥምረት የኢራኑን መሪ ከሩሲያ ጋር ኢኮኖሚያዊ እና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት እንድትመሰርት እንደገፋፋቸው ዘገባው ጠቅሷል፡፡
"ኢራን ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ከኢኮኖሚ እስከ ኤሮስፔስ እና የፖለቲካ ዘርፎች ለማሳደግ ቆርጣ ተነስታለች" ሲሉ ራይሲ ለፑቲን በስብሰባቸው ወቅት ተናግረዋል።
"በቴህራን እና በሞስኮ መካከል ያለው ትብብር በአገሮቻችን ላይ በዩኤስ ማዕቀቦች ላይ የተጣለውን ውስንነት በእጅጉ ያስወግዳል"ብለዋል።