አረብ ኢምሬትስ ፖሊዮን ለማጥፋት ለሚደረገው አለምአቀፍ ጥረት እስካሁን 1.3 ቢሊዮን ድርሃም መስጠቷ ተገለጸ
በጋዛ 640ሺ ህጻናትን ለመከተብ ዘመቻ የተከፈተ ሲሆን አረብ ኢምሬትስ ይህ ዘመቻ እንዲሳካ ድጋፍ እያደረገች ነው
የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አረብ ኢምሬትስ ፖሊዮን ለመዋጋት ለሚደረገው አለምአቀፍ ላላት አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥተዋል
አረብ ኢምሬትስ ፖሊዮን ለማጥፋት ለሚደረገው አለምአቀፍ ጥረት እስካሁን 1.3 ቢሊዮን ድርሃም መስጠቷ ተገለጸ
አረብ ኢምሬትስ ፖሊዮን ለማጥፋት በሚደረገው አለምአቀፍ ጥረት ቀዳሚ ሚና እየተወጣች እና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ በርካታ ሀገራት በተለይ በፓኪስታን ለሚገኙ ህጻናት የህይወት አድን ክትባት ለማድረስ በትኩረት እየሰራች መሆኗ ተገልጿል።
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ከ2011 ጀምሮ "ሪቺንግ ላስት ማይል" በሚለው መርሃግብር ከ1.3 ቢሊዮን ድርሃም ሰጥተዋል።
አረብ ኢምሬትስ በ2ዐ14 በፓኪስታን በጀመረችው የኢምሬትስ ፖሊዮ ክትባት ዘመቻ አማካኝነት፣ 700ሺ ክትባት ለህጻናት አሰራጭታለች። ባለፈው ነሐሴ ወር ሸክ መሀመድ ቢን ዛይድ በጋዛ ሰርጥ የመጀመሪያ የፖሊዮ በሽታ ከመተዘገ በኋላ የአስቸኳይ ጊዜ የፖሊዮ ክትባትን ለማገዝ የሚውል የ5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በጋዛ 640ሺ ህጻናትን ለመከተብ ዘመቻ የተከፈተ ሲሆን አረብ ኢምሬትስ ይህ ዘመቻ እንዲሳካ ድጋፍ እያደረገች ነው።
የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም አረብ ኢምሬትስ ለዘመቻው ድጋፍ ማድረጓን ማመስገናቸው እና ፖሊዮን ለመዋጋት የሚደረገው አለምአቀፍ ጥረት ያላትን አስተዋጽኦም ማስታወሳቸው ተገልጿል።
ዋና ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት አረብ ኢምሬትስ ድርጅቱ በአለምአቀፍ ደረጃ ወረርሽኞችን ለመዋጋት የሚያደርገውን ጥረት በተከታታይ ድጋፍ እያደረገችው ነው።
በ1988 የፖሊዮ ተጠቂዎች ቁጥር 350ሺ የነበረ ሲሆን ከአስር አመት በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ ሙያተኞች ባደረጉት ጥረት በ99 በመቶ ቀንሷል።