28ኛው የተመድ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የፊታችን ሕዳር በዱባይ ይካሄዳል
አረብ ኢምሬት ዓለም አቀፉን የባዪፊዩል ጥምረትን ተቀላቀለች።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት የአየር ብክለይን ለመቀነስ በሚል በሕንድ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ የተቋቋመውን የባዮፊዩል ጥምረት ተቀላቅላለች።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት የሀይል እና መሰረተ ልማት ሚንስትሩ ሱሄል ቢን መሀመድ አል ማዝሩዊ እንዳሉት ጥምረቱን ተቀላቅላለች።
ሚንስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሉት አረብ ኢምሬት የሀይል ምንጭ ስብጥርን ለማረጋገጥ በባዮፊዩል ልማት ላይ ገንዘብ ፈሰስ እያደረገች መሆኗን ገልጸዋል።
ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን የካርበን ጋዝ ለመቀነስ ለታዳሽ ሀይል ትኩረት መስጠቷን የተናገሩት ሚንስትሩ በሕንድ በተካሄደው 14ኛው ዓለም አቀፍ የባዮፊዩል ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል።
ሚንስትሩ በሕንዷ ጓ ግዛት በተካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ የተባበሩት አረብ ኢምሬት ልኡካንን በመምራት ተሳትፈዋል።
ሚንስትሩ አል ማዝሩዊ በዚህ መድረክ ላይ የፊታችን ሕዳር በአቡዳቢ ስለሚካሄደው ኮፕ28 ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ ጠቀሜታም አስረድተዋል።
ኮፕ28 የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በመድረኩ ለነበሩ ታዳሚያን ያስረዱት ሚንስትሩ በዱባይ በተለዋዋጭ የአየር ንብረት ለውጥ እየተፈተነች ላለችው ምድራችን መፍትሔ የሚሆኑ ውሳኔዎች እንደሚወሰኑ እና ወደ ተግባር የሚቀየሩባቸው አሰራሮች እንደሚዘረጉም ተናግረዋል።