ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ለአረብ ኢምሬት አቻቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ በስጦታነት አበረከቱ
የአረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን ለቱርኩ አቻቸው የዛይድ ክብር ሽልማትን ሰጥተዋል
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን የተባበሩት አረብ ኢምሬትስን በመጎብኘት ላይ ናቸው
ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ለአረብ ኢምሬት አቻቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ በስጦታነት አበረከቱ።
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን ለቱርክ አቻቸው ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን በሁለትዮሽ እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
የተርኪየ ፕሬዝዳንት ቶጋ የተሰኘችውን የኤልክትሪክ ተሽከርካሪ በስጦታ መልኩ ለፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህን አበርክተዋል።
ይህችን ቱርክ ሰራሽ ተሽከርካሪ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የተቀበሉ ሲሆን ሲያሽከረክሯት ታይተዋል።
የተባበሩት አረብ ኢምሬትስም የዛይድ ሽልማትን ለተርኪየ ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ሸልማለች።
የዛይድ ሽልማት በተባበሩት አረብ ኢምሬት ካሉ ለሲቪል ሰዎች ከሚሰጡ ሽልማቶች ከፍተኛው ተገልጿል።
አረብ ኢምሬት ይህን የዛይድ ሽልማት ለፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ያበረከተችው ፕሬዝዳንቱ ለቱርክ እና አረብ ኢምሬት ወዳጅነት መሻሻል ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው ተብሏል።
ቢንዛይድ የተባበሩት አረብ ኢምሬት መስራች ሰው ሲሆኑ ሀገሪቱ ከትንንሽ ግዛቶች ወደ አንድ ሀገርነት እንድትመጣ እና ህዝቦቿም የበለጸጉ እንዲሆኑ ያደረጉ ታሪካዊ መሪ ናቸው።