አረብ ኢምሬት በአምስት አህጉራት በታዳሽ ሀይል ልማት ላይ እየሰራች መሆኗን አስታውቃለች
አረብ ኢምሬት ለታዳሽ ሀይል ልማት 50 ቢሊዮን ዶላር ማፍሰሷን ገለጸች።
የ2023 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ወይም ኮፕ28 በተባበሩት አረብ ኢምሬት አዘጋጅነት ይዘጋጃል።
ሀገሪቱ ለዚህ ጉባኤ ዶክተር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃቢርን የአየር ንብረት ለውጥ ልዩ ልኡክ እና የኮፕ 28 ፐሬዝዳንት መሾሟ ይታወሳል።
ዶክተር ሱልጣን በአቡዳቢ እየተካሄደ ባለው የዓለም ታዳሽ ሀይል ልማት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር "እኛ በስድስት አህጉራት ውስጥ 50 ቢሊዮን ዶላር ፈሰስ አድርገናል" ብለዋል።
ይሁንና ይህ ገንዘብ በቂ አይደለም የሚሉት ዶክተር ሱልጣን ዓለማችን ተጨማሪ የጸሀይ ሀይል ኢንቨስትመንት ያስፈልጋታልም ብለዋል።
አረብ ኢምሬት ከዓለም አቀፉ የታዳሽ ሀይል ልማት ኤጀንሲ ጋር ያለውን ትስስር ማሳደግ ውንደምትፈልግም ዶክተር ሱልጣን በንግግራቸው ላይ ጠቅሰዋል።
የዓለምን የሀይል ፍላጎት ለማረጋገጥም አረብ ኢምሬት ከዓለም አቀፉ ታዳሽ ሀይል ልማት ኤጀንሲ ጋር ተቀራርባ መስራት ትፈልጋለችም ተብሏል።
በአቡዳቢ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው ሰባተኛው የዓለም አቀፉ የታዳሽ ሀይል ልማት ኤጀንሲ ጉባኤ ላይ በርካታ ዓለም አቀፍ የታዳሽ ሀይል ልማት ባለሙያዎች እና አመራሮች እየተሳተፉ ነው።