አቡዳቢ የተመድ አባል ሀገራት ግዛታዊ አንድነት እንዲጠበቅ ትፈልጋለች
አረብ ኢምሬትስ አሁን ላይ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለው ውጊያ እንዲቆም አቀረበች፡፡
በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ እያደረገች መሆኑን የገለጸችው ሩሲያ ወደ ኬቭ እየተቃረበች መሆኑን ያስታወች ሲሆን አሜሪካና አጋሮቿ ይህንን እንዲታቆም እየጠየቁ ናቸው፡፡ የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነት እንዲያቆመኑ ተማጽነዋቸው ነበር፡፡
አረብ ኢምሬትስ እና ቱርክ ኢንቨስትመንት ለመጨመር13 ስምምነቶች ተፈራረሙ
አረብ ኢምሬትስ ደግሞ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ ደግሞ በዩክሬን ያለው ጦርነት እንዲቆም ጥ አቅርባለች፡፡ በጦርነቱ አደገኛ ሁነቶች መምጣታቸው የዓለምን ሰላምና ጸጥታ ሊያበላሹ እንደሚችሉም የአረብ ኢምሬትስ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
አረብ ኢምሬትስ ይህንን ያስታወቀችው የተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ስብሰባ በተደረገበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል፡፡ የዩኤኢ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር በዩክሬን ያሉ ንጹሃን ጉዳይ እንደሚያሳስባት ገልጻለች፡፡
በተመድ የአረብ ኢምሬትስ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ላና ኑሰይባ ፤ ሀገራቸው ከፀጥታው ምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን ጦርነት እንዲቆም እንደምትሰራ ገልጸዋል፡፡ አምባሳደሯ አሁን ላይ ምክክር እንደሚያስፈልግ ያነሱ ሲሆን ሀገራቸው፤ ሁሉም የተመድ አባል ሀገራት ግዛታዊ አንድነት መጠበቅ እንዳለበት እንደምታምን ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የጸጥታው ም/ቤት ያቀረበውንና ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን ወረራ የሚያወግዘው የውሳኔ ሃሳብ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ውድቅ ስታደርግ ዩኤኢ ደግሞ ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል፡፡
ሩሲያ ውድቅ ያደረገችውን የውሳኔ ሃሳብ ከአረብ ኢምሬትስ በተጨማሪም ቻይና እና ህንድም ድምጽ ተአቅቦ አድርገውበታል፡፡ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡ 193 አባላት ላሉት የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ይቀርባል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል፡፡