አረብ ኢምሬትስ 35 ቶን የምግብ እርዳታ ለትግራይ ክልል መላኳን አስታወቀች
አረብ ኢምሬትስ ድጋፍ የምታደርገው ድጋፍ ለሚሹ ሀገራት እርዳታ ለማድረግ ባላት ቁርጠኝነት ነው ብለዋል አምባሳደሩ
አረብ ኢምሬትስ ባለፈው አመት 200 ቶን የአትክልት ዘይትን ጨምሮ 300 ቶን እርዳታ መቀሌ ማድረሷን ገልጿለች
አረብ ኢምሬትስ የላከችው 35 ቶን ምግብ የጫነ አውሮፕላን ወደ ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በዛሬው እለት መላኳን ገልጻለች፡፡
በኢትዮጵያ የአረብ ኢምሬትስ አምባሳደር ሞሀመድ ሳሊም አልረሽድ እንደገለጹት የተደረገው የምግብ እርዳታ በትግራይ ክልል ያለውን የሰብአዊ ሁኔታ ለመርዳት ነው ብለዋል፡፡
- የዓለም ጤና ድርጅት 33.5 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ ጀምሬያለሁ አለ
- አለምአቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ህይወት አድን እርዳታ ትግራይ ማድረሱን አስታውቀ
አረብ ኢምሬትስ ድጋፍ የምታደርገው ድጋፍ ለሚሹ ሀገራት ሰብአዊ እርዳታ ለማድረግ ባላት ቁርጠኝነት መሰረት መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡
የምግብ እጥረት ላለበት ህዝብ አስፈላጊ የምግብ ድጋፍ ለማድረግ ኢምሬትስ እንደምትሻ የገለጹት አምባሳደሩ ይህ እርዳታ የተበረከተው ኢምሬትስ አስቸኳይ እርዳታ ለመፈልጉ ሀገራት ለመድረስ ባላት ቁርጠኝነት ነው ብለዋል፡፡
አምባሳደር ሞሀመድ እንደገለጹት አረብ ኢምሬትስ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ባለፈው አመት 200 ቶን የአትክልት ዘይትን ጨምሮ 300 ቶን እርዳታ መቀሌ ማድረሷን ገልጸዋል፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ ጥቅምት 2013ዓ.ም የተጀመረው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡
ህወሓት ግጭቱን በሰላም ለመፍታት ከመንግስት ጋር በሌላ አካል በኩል እየተነጋገረ መሆኑን ቢገልጽም፣ መንግስት ግን ከህወሓት ጋር ድርድርም ሆነ ንግግር አልጀመርኩም ሲል ማስተባበሉ ይታወሳል፡፡
የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦባሳንጆ ግጭቱን በሰላም ለመፍታት ጥረት እያደረጉ ነው፤አሜሪካም በአፍሪካ ህብረት በኩል የሚደረገውን ጥሪት እንደምትደግፍ ማስታወቋ ይታወሳል፡፡
በ2013 ዓ.ም ጥቅምት ወር በትግራይ ክልል የተጀመረው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲገደሉ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ እንዲፈናቀሉ ኑሯቸው እንዲመሰቃቀል ምክንያት ሆኗል፡፡