ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ከፈረንሳይ አቻቸው ኢማኤል ማክሮን ጋር ተወያይተዋል
የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በዛሬው እለት በፈረንሳይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን ከፈረንሳይ ከፈረንሳይ ኢማኤል ማክሮን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የአረብ ኤምሬትስ የዜና አገልግሎት (ዋም) ዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት በመዳሰስ የሁለትዮሽ ትብብርን በተለይም በኢኮኖሚ፣ ኢንቨስትመንት እና የባህል መስኮች ላይ ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይ መክረዋል።
በአየር ንብረት፣በኢነርጂ፣ላቀ ቴክኖሎጂ፣አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሌሎች ዘርፎች የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል።
ሁለቱ መሪዎች በአህጉራዊ እና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን፤ በመካከለኛው ምሥራቅና ከዚያም ባሻገር ያሉትን አንገብጋቢ የሆኑ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በጋራ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አንጽዞት ሰጥተው መክረዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ-ፈረንሳይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በጋራ ለመስራ የመኪያስችላቸውን የትብብር ማዕቀፍ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በተገኙበትም ተፈርሟል።
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅትም ሁለቱ መሪዎች ስልታዊ የአርቴፊሻ ኢንተለጀንስ አጋርነት ለመፍጠር ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።