የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ለይፋዊ ጉብኝት አሜሪካ ገቡ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በዋይትሃውስ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል
የኤምሬትስ አሜሪካ ፕሬዝደንቶች በሁለት አመታት ውስጥ ለዘጠነኛ ጊዜ ነው የተገናኙት
የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ለይፋዊ ጉብኝት አሜሪካ ገቡ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በዋይትሃውስ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የፕሬዝደንቱ የአሜሪካ ጉብኝት ስልጣን ከያዙበት ከ2022 የወዲህ የመጀመሪያቸው ነው።
መሪዎቹ የሚያደርጉት ስብሰባ በሁለት አመታት ውስጥ ለዘጠነኛ ጊዜ ሲሆን የአረብ ሀገር እና የአሜሪካ መሪዎች በዚህን ያህል ድግግሞች መገናኘታቸው በሪከርድነት ተመዝግቧል።
መሪዎቹ በሚኖራቸው ውይይት በቀጠናዊ ጉዳዮች፣ በቴክኖሎጂ እና የደህንነት ትብብር ዙርያ ትኩረት አድርገው እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡
የሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ጉብኝት የአሜሪካ የረጅም ጊዜ የደህንነት አጋር ሆና የዘለቀችው ኤምሬትስ የራሷን የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ ለመገንባት የአሜሪካን ቴክኖሎጂ ለማግኘት ያላትን ፍላጎት የሚንጸባረቅበት ይሆናል፡፡
"ጂ 42" የተባለው በመንግሰት የሚደገፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የማይክሮሶፍት አጋር ከሆነው ናቪድ የማይኮ ቺፕ አምራች ተቋም ጋር የ1.5 ቢሊየን ዶላር ስምምነት ፈጽመዋል፡፡
በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ በቢሊየን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ እያደረገች የምትገኘው አቡዳቢ በኢኮኖሚ ፣ በጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ቴክኖሎጂን በሰፊው ለመጠቀም ካላት ፍላጎት በመነሳት ከዋሽንግተን ጋር የትብብር ስምምነት እንደምትፈራረም የአረብ ኤምሬትስ የዜና ወኪል ዋም ዘግቧል።
ቻትጂፒቲ እየሰጠ የሚገኘው አገልግሎት በአረበኛ እና ህንደኛ ቋንቋዎች በማበልጸግ በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን ከ አሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር መስራት እንደምትፈልግ አስታውቃለች።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ሀገሪቱን በፕሬዝዳንትነት መምራት ከጀመሩ ወዲህ በአሜሪካ ለመጀመርያ ጊዜ እያደረጉት በሚገኘው ጉብኝት በሊባኖስ ፣ በጋዛ እና ሱዳንን በተመለከቱ የደህንነት ጉዳዮች ዙርያ ከባይደን ጋር የሚመክሩ ይሆናል፡፡
አሜሪካ አረብ ኢምሬትስ እና አመራሯ ችግሮችን በመጋፈጥ እና በአለም ሰላም እና መረጋጋት እንዳፈጠር ለምታደርገው ጥረት በተደጋጋሚ አድናቆቷን ችራታለች።
ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝደንት ሼክ ሞሀመድ ቢን ዛይድ በተለይ በቀጣናዊ ልማት፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመዋጋት እና በዘላቂ መፍትሄዎች ላይ ለተጫወቱት ሚናም አሜሪካ እውቅና ሰጥታቸዋለች።
መሪዎቹ በሚያደርጉት ስብሰባ ለ50 አመታት በዘለቀው የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኘነት እንዲሁም በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ እና በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ይመክራሉ ተብሏል።