አለምአቀፍ ሚዲያዎች ስለኮፕ28 ስኬቶች የሰጡት ሽፋን
አለምአቀፍ ሚዲያዎች ታሪካዊ የተባለው 'የዩኤኢ ስምምነት' ስለተደረሰበት የኮፕ28 ስኬት በርካታ ሽፋን ሰጥተዋል
198 ሀገራት ታሪካዊ የተባለውን 'የዩኤኢ ስምምነትን' መፈረማቸው ለወደፊት የአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ትግበራ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ተብሏል
አለምአቀፍ ሚዲያዎች ታሪካዊ የተባለው 'የዩኤኢ ስምምነት' ስለተደረሰበት የኮፕ28 ስኬት በርካታ ሽፋን ሰጥተዋል።
የስብሰባውን ስኬታማነት እና የ'ዩኤኢ ስምምነትን' አስፈላጊት ከዘገቡት ዋናዋና ሚዲያዎች መካከል ሮይተርስ፣ ዘጋርዲያ፣ ፋይናንሻል ታይምስ፣ሲኤንኤን፣ ዘኢንዲፔንደንት፣ ስካይ ኒውስ፣ ሂንዱስታን፣ ኒውዝላንድ ሄራልድ፣ ዘኢኮኖሚስት፣ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ታይም፣ ዥንዋ፣ዘስታር ሲንጋፖር ስታር፣ ሊፍጋሮ፣ ቢቢሲ ወርድ ኒውስ፣ ኢፒሲ እና ሌሎች ይገኙበታል።
በስብሰባው ላይ የተወከሉት198 ሀገራት ታሪካዊ የተባለውን 'የዩኤኢ ስምምነትን' መፈረማቸው ለወደፊት የአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ትግበራ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ተብሏል።
በርካታ አለምአቀፍ ሚዲያዎች ይህ ታሪካዊ ስምምነት እንዲፈረም የማመቻቸት እና የማስተባበር ስራ ስለሰራችው አዘጋጇ አረብ ኢምሬትስ ሚናም ዘግበዋል።
ዘኢኮኖሚስት
ዘኢኮኖሚስት ጋዜጣ አለም ለመጀመሪያ ጊዜ ከነዳጅ ኃይል ወደ ታዳሽ ኃይል ለመሸጋገር ስምምነት ላይ ደርሷል ሲል ዘግቧል።
ጋዜጣው "ባለፈው ሳምንት አክቲቪስቶች እና ዲፕሎማቶች የኮፕ28 ስብሰባን ለመካፈል ለመጀመሪያ ጊዜ በዱባይ ሲገናኙ ትልቅ ስምምነት ላይ ይደረሳል የሚለው ግምት በበርካታ ምክንያቶች አነስተኛ ነበር" ሲል ጠቅሷል።
198 ሀገራት ፍትሃዊ፣ ስርአት ባለው፣ ኃላፊነት በተሞላበት እና በሂደት ከነዳጅ(ፎሲል ፊውል) ለመሸጋገር ተስማምተዋል።
ጋዜጣው ዶክተር ሱልጣን ቢን አህመድ አልጀባር ድርድሩ ስኬታማ እንዲሆን የነበራቸውን ሚና አመልክቷል።
ቢቢሲ ኔትወርክ
ቢቢሲ "ፎሲል ፊውል ላይ ኢላማ ያደረገ ታሪካዊ የኮፕ28 ስብሰባ" በሚል ርዕሱ ባወጣው ዘገባ ሀገራት ከነዳጅ እና ጋዝ ወደ ታዳሽ ኃይል ለመሸጋገር ለመጀመሪያ ጊዜ ግልጽ ግብ አስቀምጠዋል ብለዋል።
ዋሽንግተን ፖስት
ዋሽንግተን ፖስትም ሀገራት ከነዳጅ ለመሸጋገር ታሪካዊ ስምምነት ላይ ደርሰዋል የሚል ይዘት ያለው ዘገባ አስነብቧል።
ሮይተርስ
200 የሚጠጉ ሀገራት የነዳጅ ኃይል መቀነስ ለመጀመር መስማማታቸውን ዘግቧል።
ዘኢንዲፔንደንት
ይህ ጋዜጣ መንግስታት የነዳጅ ኃይላቸውን እንዲቀንሱ የሚያደርግ ስምምነት መፈረማቸውን ዘግቧል።
ዩሮ ኒውስ
የኮፕ28 ስብሰባ የነዳጅ ዘመንን ማብቃት የሚያመላክት ታሪካዊ ስምምነት መፈረሙን ዘግቧል።
ታይም መጽሄት
ታይም መጽሄት ኮፕ28 ስብሰባ አለምን ከሁሉም አይነት ታዳሽ ኃይሎች(ነዳጅ እና ጋዛ) በሚያሸጋግር በታሪካዊ ስምምነት ተጠናቋል ብሏል።
ዘጋርዲያን ኒውስፔፐር
ታረካዊውን የኮፕ28 ስምምነት 'ሽግግር' ሲል አስፈላጊነቱን ገልጿል። 200 ገደማ ሀገራት ለመጀመሪያ ጊዜ የታዳሽ ኃይል መጠቀምን ለመቀነስ መስማማታቸውን ዘግቧል።
ሲኤንኤን ኔትወርክ
"በዱባይ በተካሄደው የኮፕ28 ስብሰባ አለም የአየር ንብረት ስምምነት ላይ ለመድረስ በአንድነት ቆሟል" የሚል ርዕስ ያለው ዘገባ አውጥቷል።
ስካይ ኒውስ አሜሪካን
በኮፕ28 ስብሰባ 200 ገደማ ሀገራት ታዳሽ ኃይልን ለመቀነስ ቁርጠኝነታቸውን አሳይተዋል ብሏል።
ብሉምበርግ
በዱባይ የተካሄደው የኮፕ28 ስብሰባ የአለም መሪዎች ታደሽ ኃይልን ለመቀነስ ቁርጠኛ እንዲሆኑ በሚያስችል ስምምነት መጠናቀቁን ዘግቧል።
የስፔኑ ጋዜጣ ኢል ፖይስ
የኮፕ28 ፕሬዝደንት ዶክተር አል ጃብር ታሪካዊ ስምምነት የተደረሰበትን ስብሰባ መርተዋል። ከዚህ በፊት ከተደረሱ በርካታ ስምምነቶች በተለየ መልኩ ይኸኛው ስምምነት የቀውሱ ዋና ምክንያት በሆነው ታዳሽ ኃይል ላይ ነው ሲል ዘግቧል።