የንግድ ልውውጣቸውን ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እየሰሩ ያሉት አረብ ኢምሬትስ እና ህንድ
አረብ ኢምሬትስ ሁለተኛዋ ግዙፍ ከሆነችው የንግድ አጋሯ ህንድ ጋር ያደረገችው የንግድ ልውውጥ በ2022-23 ወደ 85 ቢሊዮን ዶላር አድጓል
ከ2022-2023 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ አረብ ኢምሬትስ የህንድ ሶስተኛው ግዙፍ የንግድ አጋር እና ለህንድ የውጭ ንግድ ሁለተኛዋ መዳረሻ መሆን ችላለች
የመካከለኛው ምስራቋ አረብ ኢምሬትስ እና ህንድ በመካከላቸው ያለውን ከነዳጅ ውጭ የሆነውን የንግድ ልውውጥ በ203ዐ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እየሰሩ ናቸው።
አሁን ላይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ እየጨመረ መጥቷል።
በቱሪዝም፣ በበረራ፣ በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች፣ በታዳሽ ኃይል፣ በቴክኖሎጂ፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በትራንስፖርት ዘርፎች ላይ ሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ እያካሄዱ ናቸው።
የአቡዳቢ አልጋወራሽ ሼክ ካሊድ ቢን ሞሀመድ ቢን ዛይድ በትናንትናው እለት ወደ ህንድ ያደረጉት ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ስትራቴጂካዊ እና ታሪካዊ ግንኙነት ጥልቅ መሆኑን ነው ተብሏል።
በሁለቱ ሀገራት በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የወሰዷቸው እርምጃዎች ሌሎች ሀገራትም እንደምሳሌ ሊወስዱት የሚገባ ነው። ሀገራቱ በፈረንጆቹ ግንቦት 22፣2022 'ኮምፕሬሄንሲቭ ኢኮኖሚክ ፓርትነርሺፕ' የተባለ የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።
ስምምነቱ አረብ ኢምሬትስ እና ህንድ ከነዳጅ ውጭ ያለውን ንግዳቸውን በ2030 ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ለማድረግ የያዙትን እቅድ ለማሳካት መንገድ የሚጠርግ ነው።
ከ2022-2023 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ አረብ ኢምሬትስ የህንድ ሶስተኛው ግዙፍ የንግድ አጋር እና ለህንድ የውጭ ንግድ ሁለተኛዋ መዳረሻ መሆን ችላለች። አረብ ኢምሬትስ ሁለተኛዋ ግዙፍ ከሆነችው የንግድ አጋሯ ህንድ ጋር ያደረገችው የንግድ ልውውጥ በ2022-23 ወደ 85 ቢሊዮን ዶላር አድጓል።
በጥቅሉ ሲታይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ከነዳጅ ወጭ ያለው ንግድ በ2022 ከነበረበት ከ51.4 ቢሊዮን ዶላር በ2023 ወደ 53.4 በሊዮን ዶላር ወይም በ3.94 በመቶ ከፍ ሊል ችሏል።
አረብ ኢምሬትስ ከ2019-23 በህንድ ያፈሰሰችው ሀብት 16.2 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ህንድ በአረብ ኢምሬትስ ያፈሰሰችው ሀብት ደግሞ 7.76 ቢሊዮን ዶላር ነው።
አረብ ኢምሬትስ ህንድ ውስጥ በታዳሽ ኃይል፣ በማዕድን፣ በሶፍትዌር፣ በአይቲ ሰርቪስ፣ በኬሚካል እና በኦርጅናል የመኪና መለዋወጫዎች ምርት እና በሌሎች ዘርፎች ኢንቨስት አድርጋለች።
በአረብ ኢምሬትስ ከሚኖሩ የውጭ ዜጎች ውስጥ ህንዶች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሲሆን ለሀገሪቱ ኢኮኖማም ገልህ አስተዋጽኦ አላቸው።