አልጋወራሹ በህንድ ዋና ከተማ ኒው ዴልሂ በሚኖራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ይገናኛሉ
አልጋ ወራሽ ሼክ ካሊድ ቢን ሞሀመድ ቢን ዛይድ ህንድ ገቡ።
የአቡዳቢ አልጋወራሽ ሼክ ካሊድ ቢን ሞሀመድ ቢን ዛይድ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው እለት ህንድ ገብተዋል።
አልጋወራሹ በህንድ ዋና ከተማ ኒው ዴልሂ በሚኖራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ይገናኛሉ።
ሼክ ካሊድ ቢን ሞሀመድ ቢን ዛይድ ከሞዲ በተጨማሪ ከህንድ ባለስልጣናት ጋር በተለያዩ ወሳኝ ዘርፎች ላይ በትብብር መስራት ስለማቻልበት ሁኔታ እንደሚመክሩ ገልጿል።
መሪዎቹ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ተጠቀሚነት በሚያረጋግጡ ዘርፎች ላይ ነው የሚመክሩት።
ሼክ ካሊድ ቢን ሞሀመድ ቢን ዛይድ በፈረንጆቹ 2023 አልጋወራሽ ከሆኑ በኋላ ህንድን ሲጎበኙ ይህ የመጀመሪያቸው ነው።
በህንድ እና በአረብ ኢምሬትስ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ነው። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህንዳውያን የመካከለኛው ምስራቅ የንግድ ማዕከል በሆነችው ዱባይ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው በመስራት ላይ ይገኛሉ።