ኤሚሬትስ በአፍሪካ የታዳሽ ሃይል ፕሮጀክቶችን ለመርዳት “ኢትሃድ 7” የተሰኘ ፕሮግራም ይፋ አደረገች
ሚኒስትሩ እንዳሉት በኢትሃድ 7 ፕሮግራም ኤምሬትስ ተመድ በአፍሪካ የሚያደርገውን የዘላቂ ልማት ግብ ያጠናክራል ብለዋል
ፕሮግራሙ በ2035 ንፁህ ኤሌክትሪክን ለ100 ሚሊዮን ህዝብ ለማቅረብ አላማ አለው ተብሏል
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (ዩኤኢ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና አለምአቀፍ ትብብር ሚኒስቴር “በአቡዳቢ ዘላቂነት ሳምንት 2022” ላይ በአፍሪካ ያሉ የታዳሽ ሃይል ፕሮጀክቶችን ፈንድ የሚያደርግ “ኢትሃድ 7” ፕሮግራም ይፋ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
“ኢትሃድ 7” በኢሚሬትስ የሚመራ የኢኖቬሽን ፕሮግራም ሲሆን አላማውም ለአፍሪካ የታዳሸ ኃየል ፕሮጅክቶች ገንዘብ ማስባሰብ ነው፡፡
ፕሮግራሙ በ2035 ንፁህ ኤሌክትሪክን ለ100 ሚሊዮን ህዝብ ለማቅረብ አላማ አለው ተብሏል፡፡
በኤሚሬትስ የውጭ ጉዳይ እና አለምቀፍ ትብብር ሚኒስቴር እና በአየር ንብረት ለውጭ ቢሮ ልዩ መልእክተኛ አስተባባሪነት መርሃ ግብሩ ከመንግስት እና ከግሉ ሴክተሮች ለንፁህ ኢነርጂ ኢንቨስትመንት ገንዘብ ይሰበስባል።
ሚኒስቴሩ ይህ ታላቅ ተነሳሽነት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከአፍሪካ ጋር ባላት የረጅም ጊዜ እና ጥልቅ ግንኙነት ላይ የሚገነባ ሲሆን ሀገሪቱ በሚቀጥሉት አስር አመታት ለአለም አቀፍ ዘላቂነት አጀንዳ ለማበርከት የምታደርገው ጥረት አካል ነው ብሏል፡፡
በመርሃግብሩ አስፈላጊነት ላይ ሃሳብ የሰጡት የውጭ ጉዳይ እና አለምቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ሸህ ሻክቡት ናህያን አልናህያን በኤሚሬትስና በአፍሪካ መካከል የኢኮኖሚ፣ባህልና ፖለቲካ እንድነት እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል፡፡
ኮፕ 28 የምታስተናግደው ኤሚሬትስ፤ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ዘላቂ ልማት እንዲኖራቸውና የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶችን በመርዳት በአጠቃላይ የቀጣናው ጤናማ እንዲሆን ለማስራት ቁርጠኛ መሆኗን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
ሚኒስትሩ እንዳሉት በኢትሃድ 7 ፕሮግራም ኤምሬትስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) በአፍሪካ የሚያደርገውን የዘላቂ ልማት ግብ ያጠናክራል ብለዋል፡፡
ሼክ ሻክቦት “በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው ጠንካራ ግንኙነት በአጋርነት እና በልማት ፕሮጄክቶች ውስጥ ተንጸባርቋል። ዛሬ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ለመላው የአፍሪካ አህጉር ብልጽግና እና ደህንነት በጥልቅ ገብተዋል።”