ኤሜሬትስ ጥቃቱ ምላሽ የሚያሻው መሆኑን በትናንትናው እለት አስታውቃለች
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሽብር ጥቃት የደረሰው የንጹሃን ሞት እና የመቁሰል አደጋ እንዳሳዘነው ገልጿል፡፡
መግለጫው ንጹሃን ጉዳት የደሰባቸውን የሲቪል ተቋማት ኢላማ ባደረገው የሽብር ጥቃት ነው ብሏል፡፡
ሚኒስቴሩ በሰብአዊነትም ሆነ በአለምአቀፍ ህግ ተቀባይነት የሌላውን የፈሪዎች ድርጊት ኢትዮጵያ እንደምታወግዝ አስታውቋል፡፡ መግለጫው የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ጉዳት የደረሰባቸው ንጹሃን በፍጥነት እንዲያገግሙ ምኞቹን ገልጿል፡፡
ሚኒስቴሩ በዚህ ፈታኝ ወቅት ኢትዮጵያ ለተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አጋርነቷን ታሳያለች ብሏል፡፡
ንጹሃንን ኢላማ አድርጓል የተባለውን የየመኑን ሆዚ የሽብር ጥቃት ያወገዘችው፣ ኤሚሬትስ ጥቃቱ አጸፋ ምላሽ የሚያሻው መሆኑን በትናንትናው እለት አስታውቃለች፡፡
የኤሜሬትስ የውጭ ጉዳይ እና አለምአቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ንጹሃንን እና ተቋማትን ኢላማ ያደረገው ጥቃት ምላሽ የሚያስፈልገው ነው ብለዋል፡፡ሚኒስቴሩ ለዚህ ሰይጣናዊ ጥቃት፣ኤሜሬትስ ለሽብር ጥቃት ምላሽ የመስጠት መብቷን ትጠቀማለች ብሏል፡፡