የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ስልጣን ከያዙ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝታቸው ፈረንሳይ ገብተዋል
የፈረንሳዩ ጉብኝት ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከያዙ በኋላ ያደረጉት የመጀመሪያ አለምአቀፍ ጉብኝት ነው
አረብ ኢምሬትስ 80 ራፋሌ የጦር አውሮፕላኖችን ለመግዛት የ14 ቢሊዮን ዩሮ ውል ከፈረንሳይ ጋር መፈራረሟ ይታወሳል
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በትናንትናው እለት ፈረንሳይ ገብተዋል፡፡
ሼህ መሀመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን በፈረንሳይ ቆይታቸው በኢነርጅ እና በትራንስፖርት መስኮች እንደሚፈራራሙ ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ሰኞ እለት በኤሊሴ ቤተመንግስት ከፈረንሳይ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች የፈረንሳይ ባለስልጣናትን ያነጋግራሉ፡፡
የፈረንሳዩ ጉብኝት ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ከያዙ በኋላ ያደረጉት የመጀመሪያ አለምአቀፍ ጉብኝት ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ በጉብኝቱ ወቅት ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ጋር በወዳጅነት ግንኙነት እና በጋራ ለመስራት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ የዜና አገልግሎት ቀደም ሲል ተናግሯል።
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በአየር ንብረት ለውጥ እና በላቀ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ጨምሮ በትምህርት፣ ባህልና እና ሁለቱን ሀገሮች ከሚያገናኘው ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ጉዳይ ይመክራሉ፡፡
ሁለቱ ሀገራት በሁሉም አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች እና የሁለቱን ሀገራት ፍላጎት እድገት እና የቀጣናውን ደህንነት እና መረጋጋት ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይወያያሉ።
አቡ ዳቢ የሉቭር ብቸኛ የውጭ ቅርንጫፍ መገኛ በመሆኑ በአረብ ኢምሬትስ እና በፈረንሳይ መካከል ያለው ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መጥቷል።
ባለፈው አመት ታህሳስ ወር አረብ ኢምሬትስ 80 ራፋሌ የጦር አውሮፕላኖችን ለመግዛት ሪከርድ የሆነ የ14 ቢሊዮን ዩሮ ውል ከፈረንሳይ ጋር መፈራረሟን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
አረብ ኢሚሬትስ በባህረ ሰላጤው ክልል ትልቁ የፈረንሳይ እና የፍራንኮፎን ስደተኞች ማህበረሰብ መኖሪያ ነው።
የባህረ ሰላጤው ኤክስፐርት አኔ ጋዴል በበኩላቸው የፈረንሳይ ጉብኝት “በእርግጥ በጣም ተምሳሌታዊ ገጽታ ያለው እና በማክሮን እና በሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ መካከል ያለውን ጥሩ ግላዊ ግንኙነት ያሳያል” ነገር ግን “በኃይል ጉዳዮች ላይ ያተኩራል” ብለዋል ። የአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አሳሳቢ በሆነበት ወቅት በሃይል ዋጋ መጨመር ምክንያት ነው።