ጆ-ባይደን የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አሜሪካ እንዲጎኙ ግብዣ አቀረቡ
ጆ-ባይደን “የሃውቲ አማጺያንን ከሽብርተኝነት መዝገብ መሰረዛቸው” የዋሽንግተን-አቡዳቡ ግንኙነት እንዲሻክር አድርጎት ቆይቷል
ጆ ባይደን እና ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በሳዑዲ አረቢያ ተገናኝተው ተወያይተዋል
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከዓመቱ መጨረሻ በፊት የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን አሜሪካ እንዲጎበኙ ግብዣ አቀረቡ።
ጀ-ባይደን ይህን ያሉት ሁለቱ መሪዎች በሳዑዲ አረቢያ እየተካሄደ ባለው የገልፍ ሀገራት-አሜሪካ የልማት እና ደህንነት ጉባዔ ላይ ባደረጉት የጎንዮሽ ወይይት ነው።
ጆ-ባይደን ለኢሚሬትስ አቻቸው "ዛሬ የሚያጋጥሙህ ፈተናዎች አብረን የምናሳልፈውን ጊዜ በጣም አስፈላጊ ያደርገዋል፤ ወደ አሜሪካ በይፋ ልጋብዝህ እፈልጋለሁ" የሚል ጥያቄ እንዳቀረቡላቸውም ነው ዋሽንግተን ፖስት የዘገበው።
ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደን በሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ለሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና ለመላው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የገለጹ ሲሆን፤ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በበኩላቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ በወቅቱ ላደረጉት ጉብኝት ፕሬዝዳንት ባይደንን እና የአሜሪካን ህዝብ አመስግነዋል።
ፕሬዝዳንት ባይደን ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን መሰናክሎችን በማስወገድ ፣ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በመፍጠር እና ከሌሎች የቀጠናው ሀገራት ጋር ትብብርን በማጠናከር ላደረጉት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አድናቆታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡
በእስራኤል እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፣ባህሬን እና ሞሮኮ መካከል አዲስ ኢኮኖሚያዊ እና የንግድ ግንኙነት ለመመስረት በሚደረገው ጥረት የአሜሪካ ሚና ምን መምሰል እንዳለበት በሚል ጉዳይም ትኩረት ሰጥተው መክረዋል መሪዎቹ፡፡
በመከላከያ ረገድም ሁለቱ ሀገራት የተጠናከረ የጸጥታ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ የቅርቡ የወንድማቸው ህልፈትን ተከትሎ በግንቦት ወር የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡
የአቡ ዳቢ ገዥ የሆኑት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ፤ በአፍሪካ ቀንድ፣ በሰሜን አፍሪካ እና ከዚያም በላይ ባሉት ፖሊሲዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር የቻሉ አንደሆኑ ይገራል።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ባስመዘገበቸው ፈጣን እድገት “ትንሿ ስፓርታ” እስከ በመባል ለሰደረሰችው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የበስተጀርባ ኃይል ናቸው ተብለው በበረካቶች የሚሞካሹ መሪ ናቸው።
ከሁለት አስርት ዓመታት በኃላ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና እስራኤል መካከል ተጋርዶ የነበረው የዲፕሎማሲ ግርዶሽ ሰብረው በመግባት አረብ ኢሚሬትስን ከአስራኤል ጋር ወዳጅነት የፈጠረች የመጀመሪያዋ የአረብ ሀገር በማድረግ በኩል ጉልህ የዲፕሎማሲ ሚና የተጫወቱ መሪም ናቸው ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ፡፡
ልክ እንደ ሳውዲ አረቢያ ሁሉ ኢሚሬትስ ከአሜሪካ የነበራት ግንኙነት ጥሩ የሚባል ቢሆንም፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን እየሻከረ መምጣቱ ይነገራል ይነገራል።
በተለይም ፕሬዝዳንት ባይደን ወደ ስልጣን በመጡበት ማግስት የየመን ሃውቲ አማጺያን ከአሸባሪ ቡድን ስም ዝርዝር ለማውጣት ያሳለፉትን ውሳኔ አረብ ኢሚሬትስ ሳያስቆጣ አልቀረም።
በውሳኔው ደስተኛ ያልሆነችው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ፤ የባይደን አስተዳደር ውሳኔውን ደግሞ እንዲያጤንና እንዲቀለብስ ስትወተውት መቆየቷም አይዘነጋም። የአረብ ሊግም በተመሳሳይ የሃውቲ አማጽያን በሽብርተኝነት እንድትፈርጅ አሜሪካን ጠይቋል።
ይህን ተከትሎም አሜሪካ የሃውቲ አማጽያንን በድጋሚ በአሸባሪነት ልትፈርጅ መሆኗ እስከ ቅርብ ጊዜ ስትገልጽ ነበር።
እናም የአሁኑ መሪዎቹ ውይይት በእነዚህ ሁሉም ጉዳዮች ላይ በመምከርና መፍትሄ በማበጀት አቡዳቢ-ዋሽንግተን ግንኙነት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ያሻግራል ተብሎ ይጠበቃል።