ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በመጀመሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው ፈረንሳይን ለምን መረጡ?
ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ የመጀመሪያ ይፋዊ ጉብኝታቸውን ዛሬ በፈረንሳይ ያደረጋሉ
የፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ጉብኝት ለገልፍ ሀገራትና ለአውሮፓ ትልቅ ትጉም ያለው ነው ተብሎለታል
የአረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ የመጀመሪያ ዓለም አቀፍ የስራ ጉብኝታቸውን ዛሬ በፈረንሳይ ማድረግ ይጀምራሉ።
ፕሬዝዳንቱ በፈረንሳይ ፓሪስ ቆይታቸው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ እና ስምምነቶችን እንደሚፈራረሙ ይጠበዋል።
የአረብ ኤሚሬት ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ነህያንን ፈረንሳይን ለጉብኝት መምረጣቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ከማጠናከር ዓለም ካለችበት ሁኔታ ጋር በተያያዘ ወቅቱን የጠበቀ እና ወሳኝ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገረሉ።
ጉበኝቱ የሁለቱን ሀገራት ጉንኙነት ማጠናከር ላይ ብቻ እንደማይታጠር የገለጹት ባለሙያዎቹ፤ ነገር ግን ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥና ለህዝቦች ዘላቂ ልማት ለማምጣት አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆኑ ትብብሮን ለማጠናከር የሚያግዝ ነውም ብለዋል
የሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ነህያንን ፈረንሳይን ለጉብኝት መምረጥ ዋነኛ ዓላማ ኢኮኖሚያዊ እና ደህንነት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የጋራ የሁለትዮሽ ግንኙትም አንዱ እንደሚሆን አንስተዋል።
የብዙ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ስትራቴጂካዊ አጋር መሆናቸው የሚገነርላቸው የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ እና ፈረንሳ፤ የጋራ ኃላፊነት ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን ለመጋፈጥ የተቀናጀ ምላሽ መስጠት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩም ይጠበቃል።
የአረብ ሀገራት የዘርፉ ባለሙያች እንደሚናገሩት ከሆነ የሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ነህያንን ፈረንሳይን ጉብኝት እና ከፕሬዝዳንት ማከሮን ጋር መወያየት ለገልፍ አውሮፓ ግንኙነት አዲስ የለውጥ ምእራፍ ሊየመጣ ችላል ተብሏል።
የአውሮፓ ህብረት የገልፍ ሀገራትን በአጠቃላይ በተለይም የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እንደ ተወካይ እና ለቀጣናው ስትራቴጂካዊ አጋር አድርጎ ስለሚቆጥራቸው በመካከላቸው ያለውን መቀራረብ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው።
በዚህም መሰረት በጉብኝቱ ላይ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ የገልፍ ሀገራትን ወክላ ፈረንሳይ ደግሞ አውሮፓን ወክል ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል።
አብደል ከሃሌክ ሰይድ የተባሉት የአረብ ፖለቲካ ተንታኝ፤ የአውሮፓ ሀገራት ከሩሲያ ጋር በገቡት እሰጣ ገባ አስቸጋሪ ጊዜያትን እያሳለፉ ነው ያሉ ሲሆን፤ በዚህ ወቅት ገልፍ ሀገራት ያሉ አጋር ሀገራት ያሰፈልጋታል፤ ለዚህም የሼክ መሃመድ ቢን ዛይግ ጉብኝት ከፍተኛ ትርጉም አል ብለዋል።
የአረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ እና የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አሁን ሲገናኙ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
የፈረንሳዩ ፐሬዝዳንት ከወር በፊት የአረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳንት የነበሩት ሼክ ከሊፋ ቢን ዛይድን ህልፈት ተከትሎ ወደ አቡዳቢ አቅንተው እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ከሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ጋር ተወያይተው እንደነበረ ይታወሳል።