ኤምሬትስ የእስያ - ፓስፊክ ግሩፕን በታዛቢነት የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ የአረብ ሀገር ሆነች
ሀገሪቱ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ እንቅስቃሴ በመግታት በሰራችው ስራ ነው የተመረጠችው
አቡዳቢ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመግታት ከሀገራት ጋር በትብብር መስራቷን እነምትቀጥል ገልጻለች
አረብ ኤምሬትስ የእስያ - ፓስፊክ ግሩፕን በታዛቢነት ተቀላቀለች።
አቡ ዳቢ የእስያ ፓስፊክ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ቁጥጥር ተቋምን በታዛቢነት በመቀላቀል የመጀመሪያዋ የአረብ ሀገር ሆናለች።
ሀገሪቱ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ እንቅስቃሴ በመግታት በሰራችው ስራ ነው የተመረጠችው።
የእስያ - ፓስፊክ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር መከላከያ ተቋም እንደ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ሽብርተኝነትን በገነዘብ መደገፍ አለማቀፍ ህግጋትን የሚያወጣው (ኤፍኤቲኤፍ) አይነት ክልላዊ አደረጃጀት ነው።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስም ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ እና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን በመግታት ረገድ ባከናወነችው ስራ የመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አሜሪካ የፋይናንስ ግብረሃይል ባለፈው ግንቦት ወር አድቆቱን እንደገለጸላት ይታወሳል።
በአለማቀፍ ደረጃ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ እንቅስቃሴን ለመግታት የሚንቀሳቀሰው ግብረሃይል (ኤፍኤቲኤፍ)ም የኤምሬትስ መንግስት አለማቀፍ መርሆዎች እንዲከበሩ በማድረግ ያሳየውን ቁርጠኝነት ማድነቁ አይዘነጋም።
ኤምሬትስ ከ44 በላይ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት የሚያስችሉ ስምምነቶችን ፈርማለች።
በበይነ መረብ የሚደረግ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠርም በ2018 ህግ ማጽደቋ ይታወሳል።
ኤምሬትስ ሽብርተኝነትን በገንዘብ ለመደገፍ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት ላከናወነችው ስራ በእስያ - ፓስፊክ ግሩፕ በታዛቢነት መምረጧ ለከወነችው ስራ እውቅና የሚሰጥ ነው ብለዋል የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ አህመድ አሊ አል ሳይፍ።
የኤምሬትስ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ተቋም ዳይሬክተሩ ሃሚድ አል ዛቢ የመሩት ልኡክም በእስያ - ፓስፊክ ግሩፕ ጉባኤ ላይ ተሳትፏል።
አቡዳቢ በቀጣይም ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ እንቅስቃሴዎች ለመግታት ከሀገራት ጋር በትብብር እንደምትሰራ አረጋግጣለች።