አረብ ኤምሬትስና ኬንያ በአየር ንብረት እርምጃ ሊተባበሩ ነው
ሀገራቱ ለአየር ንብረት ለውጥ ተግባራዊ መፍትሄዎች በሚያመጡ ሁነትች ላይ እንተባበራለን ብለዋል
አረብ ኤምሬትስና ኬንያ በ2030 የታዳሽ ኃይል አቅም በሦስት እጥፍ ለማሳደግ እንደሚተባበሩ አስታውቀዋል
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና ኬንያ በመጪው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ እና በ28ኛው የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ 28) ትብብራቸውን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።
ሁለቱ ሀገራት እነዚህ ሁነቶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለአየር ንብረት ለውጥ ተግባራዊ መፍትሄዎች ላይ በማተኮር የወደፊት መንገድ ላይ ለመስማማት እድል እንደሚሰጡ ያምናሉ።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና የአረብ ኤምሬትስ የኢንደስትሪና የላቀ ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃብር በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እርምጃው እንዲቀጥል በጋራ በሰጡት መግለጫ አሳስበዋል።
- የኮፕ28 ፕሬዝዳንት በኬንያ ከብክለት የጸዳ ቴክኖሎጂን ያስተዋወቁ ወጣቶችን አነጋገሩ
- የአየር ንብረት ፋይናንስ ጉዳይን መፍታት በኮፕ28 ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው- ዶ/ር ሱልጣን አልጃበር
ሁለቱ መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ካሉት ፈተናዎች አንዱ እንደሆነ ጠቅሰው፤ "ቀጣይ ስራ" የሚጠይቅና በናይሮቢ እና በዱባይ ለሚካሄዱ የአየር ንብረት ጉባኤዎች "ከፍተኛ ፍላጎት" እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
"የአየር ንብረት ለውጥ ዛሬ ዓለም ላይ ከተጋረጡ ታላላቅ ተግዳሮቶች አንዱ ነው። የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤም ሆነ ኮፕ 28 ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአንድነት በመሰብሰብ መፍትሄን ያማከለ እንዲሆን ወሳኝ እርምጃዎች ይሆናሉ" ሲል መግለጫው አክሏል።
ሀገራቱ ኮፕ 28ንና የአፍሪካን የአየር ንብረት ጉባኤ እውን ለማድረግ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለመስራት ቆርጠናል ብለዋል።
ጉባኤዎች ለአፍሪካ እና ለዓለም ህዝቦች እውነተኛ እና ተጨባጭ ውጤቶችን ያስገኛል በማለት ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ሩቶ የኮፕ 28 አመራር ቡድንን እንደሚደግፉ እና ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር በኃይል ሽግግር መሪነታቸውና ታዳሽ ኃይል ልማቶች ላይ ያበረከቱት ሚናንም ጠቅሰዋል።
የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ለአህጉሪቱ ወሳኝ ጊዜ ላይ የመጣ በመሆኑ ጠቃሚ ነው ብለዋል።
አረብ ኤምሬትስ እና ኬንያ በ2030 የታዳሽ ኃይል አቅም በሦስት እጥፍ ለማሳደግ እንደሚተባበሩ ተነግሯል።
ሁሉም ወገኖች በየአካባቢው ይህንን ጥረት በመቀላቀል ዓለም አቀፍ ንቅናቄን ለማነሳሳት በጋራ እንረባረብ ብለዋል።