ልዩልዩ
በአረብ ኤምሬትስ የተሰራው መንኮራኩር በተሳካ ሁኔታ ወደ ጨረቃ መጠቀ
የአረቡ ዓለም የመጀመሪያው የጨረቃ መንኮራኩር በተሳካ ሁኔታ እሁድ እለት ወደ ህዋ መጓዙ ተነግሯል
አረብ ኢሚሬትስ በጨረቃ ላይ በማረፍ አራተኛዋ የዓለም ሀገርና የመጀመሪያዋ የአረብ ሀገር ሆናለች
በአረብ ኤምሬትስ የተሰራው መንኮራኩር በተሳካ ሁኔታ ወደ ጨረቃ መምጠቁ ተገለፀ።
የአረቡ ዓለም የመጀመሪያው የጨረቃ መንኮራኩር በትናትናው እለት ጃፓን ከሚገኝ ማስንጨፊያ ማእከል የመጠቀች ሲሆን፤ ይህም በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን የኢሚሬስት የዜና ወኪል (ዋም) ዘግቧል።
በዚህም አረብ ኢሚሬትስ ከአሜሪካ፣ ሶቭየት ህብረት እና ቻይና በመቀጠል በጨረቃ ላይ በማረፍ አራተኛዋ የዓለም ሀገር መሆን የቻለች ሲሆን፤ ከአረብ ሀገራት ደግሞ የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።
በአረብ ኤምሬትስ የተሰራው ረሺድ የሚል ስያሜ የተሰጠው መረጃ ሰብሳቢ መንኮራኩር በጨረቃ ላይ የመጀመሪያ የሆነው ኤምሬትስ ተልዕኮ ሆኗል።
መንኮራኩሩ በአሜሪካ በኬፕ ካናቨራል የጠፈር ጣቢያ “ስፔስ ኤክስ ፋልኮን 9 ሮኬት” ጋር ወደ ጠፈር መጥቋል።
የመሐመድ ቢን ራሺድ የጠፈር ማዕከል እንደገለጸው የጠፈር መንኮራኩሯ ከቀጥታ አቀራረብ ይልቅ በዝቅተኛ ኃይል ወደ ጨረቃ የሚወስደውን መንገድ ትከተላለች።
ይህም ማለት ማረፊያው አምስት ወራት ያህል በመውሰድ፤ መንኮራኩሯ በፈረንጆቹ ሚያዚያ 2023 ጨረቃ ላይ ትደርሳለች ሲል የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የዜና ወኪል ዘግቧል።