የሰብአዊ መብት ጥምረት አረብ ኤሚሬትስ ኮፕ 28 የአየር ንብረት ኮንፈረንስ ለማዘጋጀት ያደረግው ጥረትና ስኬቶች አወደሰ
ጥምረቱ አረብ ኢሚሬትስ የአየር ንብረትን በመጠበቅና የአየር ንብረት ፍትህን በማስፈን ረገድ አርአያ ስራ ሰርታለች ብሏል
አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጥምረት ለተመዘገበው ስኬት የሀገሪቱን ህዝብና መንግስት አወድሷል
አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ጥምረት አረብ ኤሚሬትስ "የአየር ንብረትን በመጠበቅ፣ የአየር ንብረት ፍትህን በማስፈን እና የኮፕ 28 የአየር ንብረት ኮንፈረንስ" ለማዘጋጀት ያደረገችውን ጥረት እና ስኬቶችን አወደሰ።
የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጥምረትን ወክለው በ52ኛው ሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የጽሁፍ መግለጫ ያስገቡት ፍሌጌስ ድርጅት ሃላፊ፤ አረብ ኢምሬትስ ድርጅትን አመስግኗል።
የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጥምረትን ወክለው የጽሁፍ መግለጫ በ52ኛው የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ያቀረቡት ፍሌግስ ድርጅት ሃላፊ፤ በሰብዓዊ መብቶች እና በአየር ንብረት ዘርፍ ለተሰሩ ስራዎች አረብ ኢምሬትስን አመስግኗል።
አረብ ኤሚሬትስ የሰብአዊ መብቶችን በማክበር እና በማስተዋወቅ እንዲሁም የአየር ንብረት ፍትህን በማስፈን ረገድ ፈር ቀዳጅ ስራ እንደሰራችም አስታውቀዋል።
"የሰብአዊ መብቶችን፣ የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ የሰብአዊ መብቶችን ማስተዋወቅ እና ጥበቃን በተመለከተ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ እንዲሁም የመልማት መብት " ድርጅቱ ፍትህን ከማስፈን ጋር የተያያዙ ሁሉንም ስጋቶች እና ተግዳሮቶችን መጋፈጥ አስፈላጊ መሆኑን አመልክቷል።
የአየር ንብረት በተለይም የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በዚህ አውድ ውስጥ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመግለጫው አሳስቧል።
ጥምረቱ በትናትናው እለት አረብ ኤሚሬትስ ዜጎች እና መሪዎቻቸው በሰብአዊ መብቶች እና ነፃነቶች መስክ፣ የአየር ንብረት ፍትህን በማሳካት እንዲሁም በዘላቂ ልማት ውስጥ አበረታች ሞዴል በማቅረብ ያሳዩትን ታላቅ ስኬት አወድሰዋል።
ከ53 ሀገራት የተውጣጡ ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በውስጡ የያዘው ጥምረቱ አረብ ኢሚሬትስ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና በሰብዓው መብት አያያዝ ለውጥ ካመጡ ሀገራት ውስጥ በቀዳሚነት አስቀምጧታል።
ጥምረቱ በሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ያተኮረ ሲሆን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ስኬቶችን ላስመዘገቡ ሀገራት ሁሉን አቀፍ ወቅታዊ የግምገማ ዘዴ በመጠቀም ውጤት የሚሰጥ ነው።