አረብ ኢሚሬትስ ለአየር ንብረት ለውጥ የሚደረገው ጥረት በእጥፍ እንዲያድግ ጠየቀች
የአየር ንብረት ለውጥ የሚንስትሮች ጉባኤ በኮፐንሀገን እየተካሄደ ነው
የአረብ ኢምሬት እና ግብጽ ከፍተኛ ባለስልጣናት ዴንማርክን በመጎብኘት ላይ ናቸው
ለአየር ንብረት ለውጥ የሚደረገው ጥረት በእጥፍ እንዲያድግ አረብ ኢሚሬትስ ጠየቀች።
የአረብ ኢምሬት ኢንዱስትሪ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እንዲሁም የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃቢር ከግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ ጋር በመሆን ዴንማርክ ገብተዋል።
- “በ2030 የዓለም የበካይ ጋዝ ልቀት በ43 በመቶ መቀነስ አለበት”- የኮፕ-28 ፕሬዝዳንት
- የኮፕ-28 ፕሬዝዳንት፤ የአየር ንብረት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የምንተባበርበት ጊዜው አሁን ነው አሉ
ሚኒስትሮቹ ወደ ዴንማርክ መዲና ኮፐንሀገን ያመሩት የአየር ንበረት ለውጥ ሚኒስትሮች ጉባኤን ለመካፈል እንደሆነ ተገልጿል።
ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃቢር በመድረኩ ላይ ለአየር ንብረት ለውጥ እየተደረገ ያለው ጥረት በእጥፍ እንዲያድግ ጠይቀዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም "በኮፕ27 ላይ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የተቀመጡ ምክረ ሀሳቦችን ከመተግበር ጎን ለጎን ተጨማሪ እቅዶችን መንደፍ እና ጥረቶችን ማጠናከር ያስፈልጋል" ብለዋል።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት በየዓመቱ በየአየር ንብረት ለውጥ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክረውን ጉባኤ ታስተናግዳለች።
ይህ ጉባኤ በያዝነው የፈረንጆቹ 2023 የመጨረሻ ወራት ላይ በአቡዳቢ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።
በኮፐን ሀገን እየተካሄደ ያለው የአየር ንብረት ሚንስትሮች ጉባኤ በፈረንጆቹ 2015 በተፈረመው የፓሪስ አየር ንብረት ለውጥ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ትኩረቱን አድርጓል።