አረብ ኢምሬትስ ከተረፈ ምርት የተሰሩ ሲም ካርዶችን ለገበያ አቀረበች
ሀገሪቱ በሚቀጥለው ሳምንት የተመድ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን ታስተናግዳለች
ከቆሻሻ ተረፈ ምርት የተሰራው ሲምካርድ ለጉባኤው ተሳታፊዎች ይሰጣል ተብሏል
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ከተረፈ ምርት የተሰሩ ሲም ካርዶችን ለገበያ አቀረበች፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር ይመክራል፡፡
ይህ ጉባኤ በተመድ አባል ሀገራት እየተዟዟረ በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በተባበሩት አረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት በዱባይ ይካሄዳል፡፡
ሀገሪቱ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም አይሰጡም ተብለው የተጣሉ ተረፈ ምርቶችን ዳግም በማልማት ሲም ካርድ መስራቷን አስታውቃለች፡፡
የተሰራው ሲም ካርድ ከተረፈ ምርቶች ከመሆኑ በተጨማሪ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ እንዲሆን ተደርጎ መሰራቱም ተገልጿል፡፡
ሱልጣን አል ጀባር በታይም መጽሄት የአየር ንብረት ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ
በዚህም መሰረት 500 ሺህ ሲምካርድ መሰራቱ የተገለጸ ሲሆን የመጀመሪያው ምርቶች በቀጣይ ሳምንት ወደ ዱባይ ለሚመጡ የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ተሳታፊዎች ይሰጣል ተብሏል፡፡
እንደ ኢምሬት ዜና አገልግሎት (ዋም) ዘገባ ከሆነ በቀጣይ ሳምንት በሚመጀረው የኮፕ28 ጉባኤ ለከባቢ አየር ጤናማነት፣ የታዳሽ ሀይል ሽግግር ስለሚደረግበት፣ በካይ ጋዝ መቀነስ በሚቻልበት እና ለታዳጊ ሀገራት ድጋፍ ስለሚደርገባቸው ሁኔታዎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ በዱባይ ይመክራሉ፡፡